የሎቄ ቤተ-መንግስት
መግለጫ
መግቢያ
ከሀዋሳ ከተማ ከ6-7 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ ፊንጫዋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ይገኛል፡፡ 1951 ዓ.ም እንደተገነባ የሚነገርለት ይህ ቤተመንግስት ለቀዳማዊ ሀይለስላሴ ማረፊያነት ታስቦ የጠቅላይ ግዛቱ እንደራሴ በሆኑትና የንጉስ አንጋፋ ልጅ የሆኑት የልዕለት ተናኝወርቅ ባለቤት በሆኑት ራስ ደስታ ዳምጠው አማካይነት እንደሆነ ይነገራል፡፡
ንጉሱም ወደ አካባቢው በሚመጡበት ጊዜ ትልቁን ድርሻ እንዳበረከቱ ከቧለማሎቻቸው ጋር የሚያርፉበት በመሆኑ ለሀዋሳ ከተማ ዕድገት ትልቅ ድርሻ እንዳበረከተ በርካቶች ይስማሙበታል ፡፡ ቤተ-መንግስቱ እንዲገነባ የተመረጠው አካባቢ ከሀይቁ ዳርቻ ከመሆኑ በተጨማሪ ክረምትና በጋ የማይደርቅ ምንጭ ያለበትና መልክዓምድራዊ አቀማመጡም ሳቢና እጅግ ማራኪ ነው፡፡ቤተ-መንግስቱ ሶስት ክፍሎች ያሉት አንደ ማረፊያነት የቤት ፤የክቡር ዘበኛ ማረፊና የእንግዳ መቀበያ ሲኖሩት የንጉሱ መዋኛ ገንዳ ፤የእጣን ማጨሻና ሌሎችም አገልግሎቶች የሚካሔዱበት ስፍራ ነው፡፡(ምንጭ፡- የ2007 ዓ.ም የቱሪስት መመሪያ መጽፍ ሀዋሳ)
ታሪካዊ ፋይዳውን ስንመለከት የኢትዮጲያ ንጉሰ ንግስት በነበሩት በአጼ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት በሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ በነበሩት በራስ ደስታ ዳምጠው በ1951 ዓ.ም ለንጉሱ እና ለቧለሞቻቸው ማረፊያ ተብሎ ከሀዋሳ ከተማ 10 ከ.ሜ ርቀት ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ ፊንቸዋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተመሰረተ ፡፡
ቤተ-መንግስቱ ለቱሪዝም ያለው አስተዋጾ
- ቤተ-መንግስቱ የተገነባው የሀዋሳ ሀይቅን ተንተርሶ በመሆኑ እጅግ ማራኪ ከመሆኑም በላይ ክረምትና በጋየማይደርቁ ምንጮች ያሉበት እና አጠቃላይ አሰራሪን ስንመለከት ሦስት ክፍለ፤ች ያሉት የንጉሱ ማረፊያ ቤትና የክቡር ዘበኛ ሲኖሩት የንጉሱ መዋኛ ገንዳ፣ የእጣን ማጬሻና ሌሎችም አገልግሎቶች የሚካሔዱበት ነው፡፡በመሆኑም ከላይ የቤተ-መንግስቱ ከፍታ ቦታ ላይ በመሆኑ የሀዋሳ ከተማ ገጽታን ሙሉ በሙሉ ለመመልከት ይቻላል፡፡
- መጪው ትውልድ ቤተ-መንግስቱን በመመልከት የቀድሞ አባቶች የነበራቸውን የኪነ ህንጻ ጥበብ ይማራል፣በተጨማሪም ስላለፉት የአስተዳር አካላት ግንዛቤ ይጨብጣል፡፡