በሀዋሳ ከተማ ጉዱማሌ መግቢያ ወይም ሁሉቃ
Description
በፊጣሪ ዕለት ከሚኖሩ ሥረዓቶች አንዱ ሰውም ሆነ እንስሳት ከአሮጌው አመት ወደ አዲሱ ዓመት የመሸጋገር ተምሳሌት የሆነው መሿለኪያ/ሁሉቃ/ የመሽለክ ስነ-ሥረዓት ነው፡፡ ሁሉቃ ሁለት እርጥብ እንጨት በግራና በቀኝ ተተክሎ ይሰራል፡፡ ሁሉቃ በተገኘው እንጨት አይሰራም፡፡ በግራና በቀኝ በተተከሉ እንጨቶች ጎን ላይ እሳት እንዲነድ ተደርጎ በመሿለኪያው መራመጃ ላይ አርንጓዴ ሳር ይበተናል፡፡በዚህ ሁኔታ በተዘጋጀው ሁሉቃ ሁሉም የቤተሰብ አባላት ከብቶች ይሻገራሉ፡፡ ሁሉቃውን ሲሻገሩ የቤተሰብ አባት ከፊት ሌሎች በዕድሜያቸው ይሻገራሉ፡፡ እንስሳትም ተከትለው በሁሉቃው እንዲሾልኩ ይደረጋል፡፡ሁሉቃውን መሻገር ማለት ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት መሸጋገር አንድምታ ያለው ሲሆን በአሮጌው ዓመት የነበረው በሽታም ሆነ ችግር ለሰውና ለእንስሳት የማይመች ሁሉ ነገር ከአሮጌው ዓመት በኋላ ኩሉቃው ጀርባ ይቀራል የሚል ጽኑ እምነት ነው ያላቸው፡፡ በመሆኑም ለተለያዩጉዳይ ከአካባቢው ርቆ ያለ የቤተሰብ አባል ካለ ሥነ-ሥረዓት እንዳያመልጠው በገዜ ወደ ቀዪው ይመለሳል፡፡
በአጠቃላይ የሁሉቃ ትርጉም ከዓመት የመሸጋር ተምሳሌት ሲሆን በግራና በቀኝ የሚነደው እሳት ከአሮጌው ወደ አዲሱ ዓመት በሰላም አለፍን /ተሸገርን እንደማለት ነው ፡፡የተበተነው አረንጓዴ ሳር ደግሞ የጥሩ ዘመን ምልክት ተደርጎ ይወሳዳል ፡፡ የሁሉቃ ስነ-ሥረዓት ከተጠናቀቀ በኋላ የፍቼ በዓል አከባበር በዓል በይፋ ይጀመራል፡፡ (ወንድሞ ቶርባ፣ ፍቼ ፣ 2009፣2010፣ዓ.ም የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ)