በሐዋሳ ከተማ እና አካባቢዋ ለሁለት ቀናት የኤሌክትሪክ ሀይል መቋረጥ እንደሚኖር ተገለፀ

ይህ የተገለፀው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ደቡብ ሪጅን በፌስ ቡክ ገፁ ባወጣው መረጃ ላይ ነው።

ሪጅኑ በሐዋሳና አካባቢዋ ነገ ማለትም 08/01/2014 እና ተነገ በስቲያ በ09/01/2014 ዓ.ም ጥዋት ከ4:00-600 እንዲሁም ምሽት ከ12:00 - 2:00 ሰዓት ላይ የሀይል መቋረጥ እንደሚኖር አስታውቋል።

በእነዚህ ቀናት ስለሚኖረው የሀይል መቋረጥም መስሪያ ቤቱ ለደንበኞቹ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አስረድቷል።

በእነዚህ ቀናት ለሚፈጠረው የሀይል መቋረጥ ሪጅኑ እንደ ምክንያትም የስራ ጉዳይ ስለመሆኑ አያይዞ አስነብቧል።

የሐ/ከ/አስ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ

መስከረም 7/01/2014 ዓ.ም

ሐዋሳ

Share this Post