08
Oct
2021
ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በዛሬው ዕለት በመካሄድ ላይ ባለው 6ኛው የፌደሬሽን ምክር ቤትና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የምስረታና የመክፈቻ ጉባኤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ተሰይመዋል።
ከተለያዩ ማህበራዊ መሰረቶች የተውጣጡ የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎችም በዛሬው ዕለት በመካሄድ ላይ ያለውን የመንግስት ምስረታና የጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድን በዓለ ሲመት በሐዋሳ ከተማ ሚሊኒየም አደባባይ በጋራ በመሆን ታድመዋል።
በስድስተኛው የመንግስት ምስረታ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው በመሰየማቸው የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የተሰማቸውን ታላቅ ደስታ የገለፁ ሲሆን የለውጡ መሪ ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሐገራችን የመጣውን ለውጥ እንደሚያስቀጥሉ ያላቸውን ፅኑ እምነትም ጨምረው ገልፀዋል።
የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
መስከረም/24/2014ዓም
ሐዋሳ