በመድረኩ በሐዋሳ ከተማ በ2014ዓ.ም ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራባቸው የሚገቡ ዝርዝር ጉዳዮችን ያካተተ ቼክ-ሊስት በከተማው ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ በሆኑት በአቶ ታሪኩ ሾና የቀረበ ሲሆን ቼክ-ሊስቱ ከያዛቸው አንኳር ጉዳዮች ውስጥ በጥቂቱ:-
ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ፣የከተማ ውበትና ፅዳት፣የከተማ ገቢ፣ንግድ፣ት/ት፣የፀጥታ ስራ እንዲሁም አጠቃላይ የከተማ አጀንዳዎች ላይ ሞዴል የሆነ የቀበሌ መንደርና ብሎክ ልየታ እንደሚደረግ በዝርዝር አንስተዋል።
ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራት ጨምሮ ሌሎች ሀገራዊ አጀንዳዎችንም በንቃት መፈፀምና ማስፈፀም የአመራሩ አብይ ተልዕኮ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው ሁሉም አመራር ተግባሩን ለቅሞ መፈፀም የሚያስችለው መግባቢያ ሰነድም ከድርጅት ፅ/ቤት ጋር ይፈራረማል ብለዋል።
የውይይቱን መድረክ የመሩት የከተማው ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ካሱ አሩሳ እንደገለፁት ተግባራቱን ከአምና በተሻለ በጥብቅ የአመራር ዲሲፒሊን ካልመራን ለውጥ ለማምጣት የምንቸገር በመሆኑ ከተለመደው አሰራር መውጣትና አፈፃፀሙን ቀን በቀን መገምገም አለብን ብለዋል።
እንደ ፅ/ቤት ኃላፊው ገለፃ እስከ ብሎክና መንደር ያሉ አደረጃጀቶችን ወደ ስራ ማስገባትና ልማቱን ህዝባዊ መሠረት እንዲኖረው ማድረግ ከተቻለ ያሰብነውን ግብ ማሳካት ስለምንችል በፍፁም አገልጋይነት ስሜት የሚታይ ለውጥ እስክናመጣ ድረስ ያለ ዕረፍት መስራት ከሁላችን የሚጠበቅ ሲሆን ድርጅትም ተግባሩን እየገመገመና ግብረ-መልስ እየሰጠ ይመራል ብለዋል።
ከአመራሩ ባሻገር የየተቋሙ ባለሙያም በየመዋቅሩ እየወረደ ችግር ፈቺ ድጋፍ በማድረግ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት ይኖርበታልም ብለዋል።
የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
መስከረም/6/2014ዓም
ሐዋሳ