ቅ/ጽ/ቤቱ ከከተማ ሴክተር እና ከክ/ከተማ ለተውጣጡ ሰራተኞች የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጥቷል።
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅ/ጽ/ቤት ሀለፊ አቶ ታምሩ ተፈሪ የከተማዋ ገቢ በየጊዜው እድገት እያሰየ ቢመጣም በ2013 ዓ/ም 218 ሚሊየን
136 ሺህ 747 ብር ገቢ ሳይሰበሰብ መቅረቱን ገልጸዋል።
እንደ ሀላፊው ገለጻ በዚህም ከአንድ በላይ ደረጃውን የጠበቀ ድስትሪክት ሆስፒታል፣ 11ለሚሆኑ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ የ12 ኪ/ሜ አስፓልት እና ሌሎች የልማት ስራዎችን ሊሰራ የሚችል ገንዘብ አለመሰብሰቡን ነው የገለጹት።
አቶ ታምሩ እንደምክንያት ከተጠቀሱ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች መካከል ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ደረሰኝ አለመስጠት፣ የመረጃ አያያዝ ችግር ፣የታክስ ግዴታን በተገቢው አለመወጣት እና በሌሎችም መሆኑን አክለዋል።
የገቢ ጉዳይ ለአንድ አካል የሚተው አለመሆኑን የገለጹት አቶ ታምሩ እቅዳችንን ለማሳካት በተቀናጀ መልኩ መስራት ይገባል ብለዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የገቢ እድገት ትክክለኛነትን አረጋግጠው የፍትሀዊነትና የደረሰኝ አሰጣጥ ጉድለትና ህገወጥ ንግድ ላይ ልዩ ቁጥጥር ሊደረግ ይገባል ብለዋል።
በተሰበሰበው ገቢም ፍትሀዊ የሆነ መሰረተ ልማት እንዲኖር የጠየቁት ተሳታፊዎቹ በተቀናጀ መልኩና የመጀመሪያ አጀንዳ አድርጎ ለመስራትም በመድረኩ ቃል ገብተዋል።
ከተሳታፊዎቹ ለቀረቡ ጥያቄዎችም ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶበታል።
የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
መስከረም 13/2014 ዓ/ም
ሐዋሳ