ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን በመግታት የህዝቡን ደህንነት በማስጠበቅ ለከተማው ኢኮኖሚ ዕድገት ትኩረት በመስጠት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ

የሐ/ከ/ አስ/ የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

‎ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም

‎ሐዋሳ፣

ይህ የተገለጸው የሐዋሳ ከተማ የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ህገ-ወጥ ንግድን የሚከላከል ግብረ-ኃይል የ2017 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም ግምገማና የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ግምገማ መድረክ በደረገበት ወቅት ነው።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተክሌ ጆንባ እንደገለፁት ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን በመግታት የህዝቡን ደህንነት በማስጠበቅ ለከተማው ኢኮኖሚ ዕድገት ትኩረት በመስጠት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ከንቲባው በምግቦች ውስጥ ባዕድ ነገሮችን ቀላቅሎ መሸጥ፣ በኮንትሮባንድ ንግድ፣ ያለፈቃድ መነገድ፣ እንዲሁም ህገ-ወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩትን ነጋዴዎች ከተማ አስተዳደሩ በትኩርት እንደሚሰራና ህገ ወጦችም በህግ አግባብ እንደሚጠየቁም ገልፀዋል።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አገና ኔቶ በንግግራቸው በከተማው የገበያ ሁኔታን ህጋዊ በማድረግ የነጋዴውን እና የሸማቹን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ሸማቹ መብቱን አውቆ ንጋዴው ደግሞ ግዴታዉን በአግባቡ የሚወጣበትን ስርዓት በመዘርጋት በሸማቹና በነጋዴው መካከል ጤናማ ሁኔታ የመፍጠር ስራም እንደተሠራ ገልፀዋል።

ከንግድ ስርዓት ውጪ በህግ-ወጥ ንግድ፣ አልባሳትና ነዳጅ ጨምሮ 11 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት በመያዝ ገቢ መደረጉን ገልፀው ከዚህ ውስጥ ነዳጅ ንግድ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 2.5 ሚሊዮን ብር ለመንግስት ገቢ መሆኑን ኃላፊው ገልፀዋል።

ኃላፊው ምንም እንኳን ካለው ፍላጎት አንፃር አቅርቦቱ ላይ እጥረት ቢኖርም የቀረበውን ነዳጅ በአግባቡ ከማሰራጨት ረገድ ሌት ከቀን በመስራት እጅግ አበረታች ውጤት መመዝገቡንም ጠቁመዋል።

በመድረኩ የተገኙት ግብር -ኃይል አባላት በሰጡት አስተያየት በየዘርፋ የሚሰሩ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር ሰፊ ሥራ እንደተሠራ ከዚህም መካከል ባእድ ነገር ተቀላቅሎ ለገበያ የሚያቀርብ ነገዴዎች በህግ አግባብ እንዲጠየቁ የማድረግና የኮንትሮባንድ ስራ በሰፊው እንደተሰራ ተናግረዋል።

Share this Post