በተፈጥሯዊ መንገድ የሚዘጋጅ ኮምፖስት ከምርታማነተ በተጨማሪ ለአፈር ለምነት አጅግ ጠቃሚ መሆኑን የሐዋሳ ከተማ ግብርና መምሪያ ገለጸ።

መምሪያው የአፈር ለምነትን ለማሻሻል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ላይ የንቅናቄ መድረክ አዘጋጅቷል።

በመድረኩ ከሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ ከ12 ቀበሌያት የተውጣጡ የግብርና ባለሙያዎች፣ የጽ/ቤት አመራር ፣ በአፈር ለምነት ላይ የሚሰሩ ፣ የመምሪያው ባለሙያዎች ፣ አመራር፣ ዳይሮክተሬትና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አበባየሁ ላሊማ የአፈር ለምነት፣ በቫዬ ፈርትላይዘር እና ቪርሚ ኮምፖስት(የተፈጥሮ ማዳበሪያ) ምንነትና አጠቃቀም ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል።

ቨርሚ ኮምፖስት(ተፈጥሯዊ ማዳበሪያን) ፣ አርሶ አደሩ እንዴት ማዘጋጀት እንደሚችል እና ጥቅሙንም ጭምር በማስረዳት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የተዘጋጀ መሆኑንም ገልጸዋል።

ለጥራጥሬ ሰብሎች፣ ለጓሮ አትክልት፣ እና ለሌችም ጥሩ ምርት የሚያስገኝ ተፈጥሯዊ ኮምፖስት መሆኑንም ነው አቶ አበባው ያከሉት።

ምንም ወጪ ሳያስፈልግ በአካባቢው ከሚገኝ ደረቅ ቅጠላ ቅጠል፣ ፍግ፣ ከእንስሳት ተረፈ ምርት እና ሌሎችንም በመጠቀም ትላትሎች ከተመገቡ በኋላ የሚገኝ ምርጥ ኮምፖስት መሆኑን ሀላፊው አስረድተዋል።

እንደ አቶ አበባየሁ ገለጻ አርሶ አደሩ ማዳበሪያን ከገበያ ከመግዛት እራሱ ማዘጋጀት መቻሉ ወጪ የሚቀንስና ለአፈር ለምነትም እጅግ ተመራጭ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህ አዘገጃጀትም ለማንኛውም ሰብል የሚጠቅም ሲሆን ለ1 ሄክታር ከ5 እስከ 10 ቶን ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ይህንንም በተገቢው መንገድ በማዘጋጀት ማስቀመጥና መጠቀም የሚቻል መሆኑን የገለጹት አቶ አበባየሁ ስራው በባለሙያ ተደገ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ይህንኑ ተግባር የጀመሩ አርሶአደሮቾን ለመመልከት ወንዶገነት ወረዳ አሩማ ቀበሌ በመሄድ መመልከት ተችሏል።

በማህበርና በግል የሚሰሩ አርሶ አደሮችን መመልከት የተቻለ ሲሆን ሞዴል የሆኑ አርሶ አደሮችም ይገኙበታል።

አርሶ አደር አቶ አሰፋ አምቦ እና ሴት አረሶ አደር ወ/ሮ ዎምኢቱ ቡሽራ የዘርፉን ውጤታማነት በማየት ከራሳቸው አልፎ በስሮቻቸው ለ28 አርሶ አደር ማሰልጠን መቻላቸውን አስረድተዋል።

በ1 ወር ውስጥ ከትሎቹ ሽያጭም አንድ መቶ ሺህ ብር ማግኘታቸውን አቶ አሰፋ ገልጸዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ሚያዝያ 5/2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post