የሐ/አ/የመ/ኮሙ/ጉዳ/መምሪያ
ጥር 16/2016ዓ/ም
ሐዋሳ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሐዋሣ ከተማ አስተዳደር የ6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ፈተናዎች የተማሪዎች ዉጤት ማሻሻል ላይ ያተኮረ የዉይይት መድረክ በከተማ አስተዳደሩ ባሉ ሁሉም ት/ት ቤቶች ተካሂዷል።
በመድረኩ የሐዋሣ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ብርሃኑ ደሣለኝ እና የከተማዋ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ ምርጫዬ ደመቀ ተገኝተዋል።
የሐዋሳ ከተማ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ ዶክተር ብርሀኑ ደሳለኝ የዉይይቱ መነሻ በ2015 የትምህርት ዘመን በ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል የታዩ የዉጤት ያያዥ ጉዳዮች መነሻ መሆናቸዉን ገልፀዉ ለተማሪዎች ዉጤት መሻሻል ባለድርሻ አካላት ሁሉ የተሳተፉበት መሆኑንም አስታዉቀዋል።
ዶ/ር ብርሃኑ አክለዉም በተለይም የተማሪዎች የዕዉቀት አባት ከሆኑ መምህራን ጋር ዉይይት ማድረጉ ለተማሪዎች ዉጤት መሻሻል አይነተኛ አስተዋፆ ያበረክታል ብለዋል።
በ18ኛዉ የሐዋሣ ከተማ የትምህር ጉባኤ ላይ የተነሱ ሃሳቦችና አስተያየቶችም የዚሁ ጉዳይ ማጠናከሪያ ናቸዉ ያሉት ዶ/ር ብርሃኑ ለዉጤታማነቱም ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲረባረቡ ጥሪ አቅረበዋል።
የዉይይቱ ተሳታፊ መምህራንም በበኩላቸው የተማሪዎች ዉጤት ማሽቆልቆል ከማንም በላይ እንደሚያስቆጫቸዉ ተናግረው ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ጋር ራሳቸዉን በማስተሳሰር የድርሻቸዉን ሁሉ እንደሚወጡ በመግለፅ በትምህርት መምሪያ በኩልም ተገቢዉ ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በሚቀጥሉት ሁለት ቀናትም ዉይይቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ተማሪዎች እና ወላጆችም እንደሚሳተፉበት ተነግሯል።
All reactions:
57Negash Yacob, Semu King and 55 others