በስልጠና በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የሐዋሳ ከተማ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ደስታ ዳንኤል ስልጠናውን ባግባቡ ትኩረት ሰጥቶ የቀረበ ሲሆን በየትምህርት ቤቱ አስፈላጊውን ችግር ፈቺ ስትራቴጂክ እቅድ በማቀድ ውጤታማ የሆነ አሰራርን የሚቀርፅ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ትምህርት ቤቶቹ ባለፈው ሦስት አመታት እቅድ በማቀድ ስራው የተከናወነ ሲሆን በነዚህም ዓመታት የሚስተዋሉ ችግሮችን በመለየት ለቀጣይ ሦስት ዓመታት በእቅዱ መነሻ ችግር ፈቺ ስራዎችን መነሻ በማድረግ እንዲሰሩ እገዛ እንደሚያደረግላቸው አቶ ደስታ ተናግረዋል።
የትምህርት ጥራት ላይ ያለውን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ በመንግስት ብቻ የሚፈጸም ባለመሆኑ የሕብረተሰብ ተሳትፎ ከታከለበት እቅዱን በሚገባ ማሳካት እንደሚቻል ነው አቶ ደስታ የገለፁት።
በመምሪያው የትምህርት ቤቶች መሻሻል ዳይሬክቶሬት አቶ ሀይሉ ላንቃሞ በበኩላቸው ስልጠናው በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚስተዋሉ ችግሮችን በጥናት በመለየት በቀረበው እቅድ መሰረት ላይ ስልጠና እየተሰጠ እንደሆነ ገልፀው።
በትምህርት አስተዳደር እንዲሁም በተማሪዎች ስነ-ምግባርና ውጤታማነት ላይ በእቅድ መሥራት ተጨባጭ ለውጥ እንዳለው አቶ ሀይሉ ጨምረው ገልፀዋል።
አቶ ሀይሉ አክለውም በከተማችን ውስጥ የትምህርት ተደራሽነት እና ጥራት ለማምጣት መምሪያው ከትምህርት ዘርፉ አካላት ጋር በቅርበት እና በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የስልጠናው ተሣታፊዎች እንደተናገሩት የእቅድ ክንውን ስልጠና መሰጠቱ የትምህርት ስራውን የበለጠ ተግባር ተኮርና ውጤታማ በማድረግ የመማር ማስተማሩን ስራ የሚያሳልጥ በመሆኑ አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል።
በስልጠናው ሁለተኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ከሐዌላ ቱላ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ለተውጣጡ ርዕሰ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮችና የመምሪያው የማኔጅመንት አባላት ተሣታፊ ሆነዋል።
የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ሰኔ 13/2014/ዓም
ሐዋሳ