6ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ውጤትን ተከትሎ የተለያዩ የስራ ስምሪቶች ለአመራሩ ተሠጥቷል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በ6ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ውጤት መሠረት ከትናንት በስቲያ የክልሉን ፕሬዚደንት ሹመት ጨምሮ የክልሉን ካቢኔ በመሾም አዲሱን የክልል መንግስት በተሳካ ሁኔታ መመስረቱ ይታወቃል።

ክልሉ አዲሱን የመንግስት ምስረታ ባከናወነ ማግስት አሸናፊው የብልፅግና ፓርቲ ባደረገው የአመራር ምደባና ስምሪት አቶ አብርሀም ማርሻሎን የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ፣አቶ አስፋው ጎኔሶን የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ፣ አቶ አሸናፊ ኤልያስን የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም አቶ የኃላዕሸት በቀለን የሲቪክ ተቋማትና የፖለቲካ ፓርቲዎች ክትትል ዘርፍ ሀላፊ ሆነው እንዲቀጥሉ ወስኗል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

መስከረም 22/2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post