የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህጻናት እና ወጣቶች መምሪያ በአለማቀፍ ደረጃ ለ32ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ16ኛ ጊዜ " ሀገር የምትገነባው ለዛሬዎቹ ህጻናት በምንሰጠው ትኩረት ነው" በሚል መሪ ቃል ከህጻናት ፖርላማ አባላት እንዲሁም ጥሪ ከተደረገላቸው እንግዶች ጋር አክብሯል፡፡
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህጻናት እና ወጣቶች መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት ወ/ጻዲቅ በዚህ መድረክ ላይ ለህጻናት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት በመሆኑ በዙሪያችን ያሉ ህጻናትን በመጠበቅና በመንከባከብ የዜግነት ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል ያሉት ብለዋል።
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ካሰች ተፈራ በበኩላቸው የዘንድሮውን ዓለም ዓቀፍ የህፃናትና ቀንን ሲከበር የተጋረጠብን ፈተናና ችግር ተሻግረን ለህፃናት ምቹ ሀገር ለመገንባት እንዲሁም የሴቶችን መብት በማስጠበቅ ከጥቃት በመከላከልና አጋርነታችንንም በማሳየት ሊሆን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
የመምሪያው የሴቶችና ህጻናት መብትና ደህንነት ማስጠበቅ ዳይሬክቶሬት የሆኑት ወ/ሮ ወይንሸት ብርሃኑ በህጻናት ስነ- ምግባርና ከማሳደግ አንጻር ስለሚጠበቁ ተግባራት ዙሪያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በሰነዱም ላይ ውይይት ተደርጓል።
የፕሮግራሙ ተሣታፊዎች የሆኑት ህጻናት በበኩላቸው ሴቶችና ህፃናትን ከጥቃት መጠበቅ መብቶቻቸውን ማስከበርና ተሳፎአቸውን ለማሳደግ ትኩረት በመስጠት ሊሠራ ይገባል በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በፕሮግራሙ ማጠናቀቂያ ላይም ለጀግናው የሀገር መከለከያ ሠራዊትን ጧፍ በማብራት የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ህጻናትና የሰራዊቱ ቤተሰቦች የአልባሳትና የፍጆታ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረጓል።
የሐ/ከ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ህዳር 11/ 2014 ዓ.ም
ሐዋሳ