ስራዎችን በካይዘን ፍልስፍና ተግባራዊ ማድረግ ውጤታማ እንደሚያደርግ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ገለጸ።

ለመምሪያው ሰራተኞች በካይዘን ፍልስፍናና በአጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ደስታ ዳንኤል ምቹ የስራ ቦታን በመፍጠር ሰራተኛው ጥሩ ቆይታ ኖሮት ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችል የካይዘን ፍልስፍና አንዱ የለውጥ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል ብለዋል።

አቶ ደስታ ስራዎችን ማዘመን ብክነትን፣ጊዜንና ጉልበትን የሚቀንስ መሆኑን ተናግረው የተቋሙን ውጤታማነት ከፍ ለማድረግ ስልጠናው ወሳኝ ነውም ብለዋል።

በቀጣይም ስልጠናው በትምህርት ቤት ደረጃ እንደሚሰጥ ነውም አቶ ደስታ ያከሉት።

ሰልጣኝ የመምሪያው ሰራተኞች በበኩላቸው ያገኙት ግንዛቤ ስራዎችን በትኩረትና በጥራት ለመፈጸም አጋዥ መሆኑን ተናግረዋል።

ሰራተኞቹ አክለውም ዘመናዊና ሳይንሳዊ አሰራሮችን መከተል እንደ ግልም ሆነ እንደተቋም ውጤታማነቱ የማያጠያይቅ መሆኑንም ነው የገለጹት።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

መስከረም 19/2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post