በሐዋሳ ከተማ ለንግድና ለመኖሪያ የሚሆኑና ለጨረታ የቀረቡ 278 ቁራሽ መሬቶችን ለተጫራቾች ለማስተላለፍ የጨረታ ሰነድ የመክፈት ስራ ተከናውነ።

በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ለንግድና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ 278 ቁራሽ መሬቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለተጫራቾች ለማስተላለፍ የጨረታ ሰነድ የመክፈት ስራ በዛሬው ዕለት ተከናወኗል።

አቶ ሚልክያስ ብትሬ በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት መምሪያ ኃላፊ በሐዋሳ ከተማ የለሙ መሬቶችን በግልፅ ጨረታ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ የማድረግ የረዥም ጊዜ ልምድ እንዳለ የገለፁ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ለ16ኛ ዙር በተካሄደ ግልፅ ጨረታ 278 የለሙ ቁራሽ መሬቶችን ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ የጨረታ ሰነድ የመክፈት ስራ መከናወኑን ገልፀዋል።

ለተከታታይ 12 ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ማስገባታቸውን የገለፁት የ16ኛው ዙር የጨረታ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደስታ ሌላሞ በታቦር፣ በመሐል ከተማ፣ በሐይቅ ዳር እና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች ለንግድና ለመኖሪያ የሚሆኑ 278 ቁራሽ መሬቶች የተዘጋጁ መሆኑን ጠቁመው 10 ሺህ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ማስገባታቸውንም ጠቁመዋል።

ግልፅ እና ተዓማኒነት ባለው የጨረታ ሂደት መሳተፋቸውን በሂደቱ የዝግጅት ክፍላችን ያነጋገራቸው በጨረታ የተወዳደሩ ተጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍሎች የገለፁ ሲሆን ካለው የጨረታ ተሳታፊ ቁጥር አንፃር የአቅርቦትና የፍላጎት አለመጣጣም መኖሩንም አመላክተዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ጥቅምት/12/2014

ሐዋሳ

Share this Post