11
Jan
2022
ረ/ኘሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ የገና በዓልን ምክንያት በማድረክ በከተማዋ ለተለያዩ የዘማች ቤተሰቦች እና አቅም ላነሳቸው ወገኖች ድጋፍ አደረጉ።
እነዚህ ወገኖች በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ በማሰብ ዘይት፣ ዱቄትና የበግ ስጦታ ነው ከንቲባው ያደረጉት።
ይህ ድጋፍ ከከተማዋ ባለሀብቶች እና ከከተማ አስተዳደሩ የተደረገ መሆኑንም ከንቲባው አክለዋል።
ሁሉም ሰው በአቅራቢያው ያለውን ከተመለከተ እና ከተደጋገፈ ችግሮችን በቀላሉ ማስወገድ እንደሚቻልም አስረድተዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ታህሳስ 28/ 2014 ዓ/ም
ሐዋሳ