በBSC እና በካይዘን ፍልስፍና ያገኙት ግንዛቤ ለውጤታማነት እንደሚያበቃቸው የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ሰራተኞች ገለጹ።

ለተቋሙ ሰራተኞች በBSC እና በካይዘን ፍልስፍና ዙሪያ ለሁለት ቀናት የቆየ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

ሰራተኞቹ በBSC አተገባበር ላይ በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ሲገልጹ በተለይም ከእቅድ ዝግጅት፣ ከምዘና አሰጣጥና በሌሎችም ተግባራት ጋር ተያይዞ የነበረብንን የእውቀት ውስንነት የሚቀርፍ ነው ብለዋል።

በካይዘን ትግበራም ያገኙት ግገንዛቤ ለግል ህይወታቸው ጭምር የሚረዳ መሆኑን የገለጹት ሰራተኞቹ እያንዳንዱ ፈጻሚ ሚናውን ለይቶ ፣ ከጊዜ፣ ከፍጥነትና ከውጤታማነት አኳያ እንደተቋም፣ እንደከተማ፣ ብሎም እንደሀገር ለውጥ ለማምጣት የሚረዳን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ አዳነ አየለ እና የመምሪያው ምክትልና የትራንስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አበራ አዴላ የ2014 ዓ/ም የተቋሙን አፈጻጸም ከፍ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም ተቋሙ አገልግሎት ሰጪ ተቋም እንደመሆኑ ሰራተኞች አይነተኛ ለውጥ እንዲያመጡና የተገልጋይ እርካታን እንዲያረጋግጡም መሆኑን ነው ሀላፊዎቹ ያከሉት።

ካይዘን ብክነትን፣ ብልሽትን ከመቅረፍ አኳያ አማራጭ የሌለው መሆኑን ገልጸው የተቋሙን የውስጥ አደረጃጀት ለማስተካከልም ኮሚቴ መቋቋሙን አሳውቀዋል።

ለውጥ እንዲመጣ ከሆነ ከአስተሳሰብ ጀምሮ መለወጥ እንደሚያስፈልግ የገለጹት ሀላፊዎቹ ዘመናዊና ሳይንሳዊ አሰራርን ተከትሎ ለአንድ አላማና ግብ በአንድነት በመስራት ለውጥ ማምጣት ከሰራተኛው ይጠበቃል ብለዋል።

ስልጠናው ቀጣይነት እንደሚኖረውም ነው ከመድረኩ የተገለጸው።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

መስከረም 15/2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post