21
Nov
2021
ኢትዮጵያ የገጠማትን ፈተና የመወጣት ብቃት አላት!!
ኢትዮጵያ የገጠማትን ወቅታዊ ፈተና የመወጣት ሙሉ ብቃት እንዳላት ኬንያ ለአሜሪካ ገለፀች።
የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር አምባሳደር ሬይሼል ኦማሞ ከአሜሪካው አቻቸው ጋር ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህ ወቅት ውጭ ጉዳይ ሚ/ር አምባሳደር ሬይሼል ኦማሞ “ኬንያ በኢትዮጵያ ተስፋ አትቆርጥም” በማለት የገለጹ ሲሆን አሁን ላይ የገጠማትን ፈተናም የመወጣት ሙሉ ብቃት እንዳላት ኬንያ እምነቷ መሆኑን አስረድተዋል።
“ኢትዮጵያን ወደቀደመ ሠላሟ መመለስ ይቻላል፤ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያዊያን ዕርዳታ ማድረስም ይቻላል፤ ነገር ግን ከሁሉ አስቀድሞ ኢትዮጵያ ችግርን የመፍታት ጥበብ እንዳላት መቀበል ያስፈልጋል” ብለዋል አምባሳደር ሬይሼል ኦማሞ።
“ዘለቄታዊ መፍሄ የሚመጣው ከውጭ ሳይሆን ከእራሳቸው ከኢትዮጵያዊያን ነው። ኬንያ እንደጥሩ ጎረቤት ማድረግ የምትችለው ኢትዮጵያ እርዳታችንን ስትፈልግና ስትጠይቅ እጃችንን መዘርጋት ነው።
ጦርነቱ ለዘላለም አይቀጥልም። ሲጠናቀቅ የምናውቃት ኢትዮጵያ ትቀጥላለች። ነገር ግን እባካችሁ በኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ በጭራሽ ተስፋ እንዳንቆርጥ።
ሁላችንም ቀና አረዳድ እና አተያይ ይኑረን” በማለት ውጭ ጉዳይ ሚ/ር አምባሳደር ሬይሼል ኦማሞ ተናግረዋል።
ምንጭ፦ ኤርትሪያ ፕሬስ አማርኛ