መድረኩን የመሩት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ተክሌ ጆንባ እና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማራዶና ዘለቀ ናቸው። ‎‎በመድረኩ ከሁሉም ማህበራዊ መሠረት የተወጣጡ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

መድረኩን የመሩት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ተክሌ ጆንባ እና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማራዶና ዘለቀ ናቸው።

‎‎በመድረኩ ከሁሉም ማህበራዊ መሠረት የተወጣጡ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

‎‎የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከህዝብ የተነሱ ጥያቄዎች ትክክለኛ መሆናቸውን አንስተው የተነሱ ጉዳዮችን እስከ ቀበሌ ወርዶ ምልከታ በማድረግ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጥያቄዎችን ቅድሚያ ሰጥተው እንደምሰሩ በመግለፅ ሁሉም ችግሮች በአንድ ጊዜ እንደማይፈታ ግንዛቤ መያዝ ያስፈልጋልም ብለዋል።

‎‎የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብር አቶ ተክሌ ጆንባ ከህዝብ ጋር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት በመግለፅ ህዝብን ለመስማትና ለማገልገል ያላቸውን ቁርጠኛ አቋም ተናግረዋል።

‎‎አክለውም ክቡር ከንቲባ አቶ ተክሌ በክ/ከተማ ውስጥ በተለያየ ምክንያት ተጀምሮ በቆሙ በነባሪ ኘሮጀክቶች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩና ሁሉም የበኩሉን በማድረግ ለከተማ ልማት ድርሻውን መወጣት እንዳለበትም ተናግረዋል

‎‎አያይዘውም ክቡር ከንቲባ አቶ ተክሌ ጆንባ ሁሉንም ጥያቄ ለመመለስ ገቢን መሰብሰብና ሀዋሳን ለኑሮ ሚቹ ጽዱና ሳቢ ከጨለማ ነፃ ማድረግ ያስፈልጋል በማለት መልዕክታቸውን አስተላፈዋል።

‎‎የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማራዶና ዘለቀ በበኩላቸው ከህዝብ ጋር በየወቅቱ ውይይት ማድረግ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን አንስተው የተነሱ ጉዳዮች ያሉ ጉዳዮች መሆናቸውንና በአጭር ፣በመካከለኛና በረዥም ጊዜ ተለይቶ በማቀድ ምላሽ እንደሚሰጣቸውም ተናግረዋል።

‎‎አክለውም አቶ ማራዶና መንግስት ከህዝብ ገቢ ሰብስቦ ለህዝብ ልማት እንደሚሰራ አንስተው የተጀመሩ ኘሮጀክቶችን ለመጨረስ፣የህዝብን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስና የተለያዩ ልማቶችን ለመስራት መደበኛና ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢን በአግባቡ ለመንግሥት እንዲገባ ማድረግ ያስፈልጋልም ብለዋል።

‎‎አያይዘውም አቶ ማራዶና በክ/ከተማ ለብዙ አመታትን የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ የቆየውን የመንገድ ከፈታ ስራ በመንግስትና በህዝብ ተሳትፎ ምላሽ እንዳገኘ በማንሳት አሁንም በሁሉም ልማት ህዝብ ማሳተፍ እንደሚገባም ገልጸዋል።‎

‎ከህዝቡ የተነሱ ጉዳዮች የውሃ ተደራሽነት፣የመንገድ ከፈታና ጥገና፣የመብራት ዝርጋታ፣በአንዳንድ አከባቢ ጎርፍ እያስከተለ ያለውን ችግር፣ከወዮ እስከ ቱላ ያለው አስፓልት መንገድ ለብዙ አመታት ተጀምሮ የቆመ፣ በትምህርት ቤቶች ተጀምሮ የቆሙ ኘሮጀክቶች፣1ኛ ና 2ኛ ደረጃ የትምህርት ቤት ተደራሽነት ጥያቄ ፣የድልድይ ጥያቄ፣ከማዞሪያ እስከ ቱሎ ያለው አስፓልት መንገድ ጉዳይ፣የወጣቶች ስብዕና ግንባታ ማዕከል ጥያቄ፣የጤና ተቋም ግንባታ ጥያቄ፣‎

‎በመድረኩ ‎ወጣቶች የመንግስት የጀርባ አጥንት በመሆናቸው መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥተው እየተሰራ እንደሆነና ወጣቶችም መንግስት ያመቻቸውን እድል በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋልም ተብለዋል።

‎ምንጭ :-‎የሀዌላ ቱላ ክ/ከ/መ/ኮ/ጽ/ቤት

Share this Post