Description

ወልደአማኑኤል ዱባለ በሲዳማ ዞን በወንሾ ወረዳ ገጃባ ቀበሌ ገበሬ ማህበር አቱካ በተከለ መንደር ከእነታቸው ሻቀጣ ጋዳዮ ከአባታቸው በራንባራስ ዱባለ ሀንካርሶ በ1923 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ በአፄ ኃይለ ስላሴ ዘመን በሲዳማ ብሄረሰብ ላይ ይደረስ የነበረውን ግፍና በደል በጽናት ይታገሉ የነበሩት እኒህ የህዝብ ልጅ ትግላቸውን በተሻለ መንገድ ለማራመድ ከ1954-1965 ዓ.ም ድረስ በዕለት ዘሮች ፖርላማ ተመርጠው የህዝብ እንደራሴነታቸው የተወጡ ሲሆን በህግ መወለኛ መምሪያ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል፡፡

በተለያየ ክ/ሀገራት በክፍተኛ ፍ/ቤት ዋና አስተዳደሪ የነበሩ ሲሆን ከአምባገነናዊ የደረግ ሥርዓት ጋር መግባባትና ህዝባቸውን መጥቀም ባለመቻላቸው ከ1970 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ ወደ ሱማሌ በርሃ በመለድ በተደራጀ የተጥቅ ትግል የደረግን መንግስት ፊት ለፊት በመጋፈጥ ከ20,000 በላይ ወታደር በማደራጀትና በማስታጠቅ ለስርዓቱ መወደቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አልተከተዋል፡፡ በበርሃ ቆይተው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ሲአን የተባለ የፖለቲካ ፖርቲ በመመስረት ለሲዳማ ህዝብ የነጻነት ሲታገሉ ቆይተው ህዳር 10/2000 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ምንጭ(አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ፣ወ/ሮ ዝናሽ ፀጋዮ፣አቶ ገረመው፣ጋር፣አቶ ደሳለኝ ጋርሳሞ፣አቶ በየነ ባዳ(2003)ዓ.ም ሲባቱመኮ፡፡አርታኢዎች ኤቶ ሱራፊል ገልገሎ፣አቶ ድሉ ሻለቃ፣አቶ ዮሐንስ ባታሞ፣አማካሪዎች፣ፕሮፊሰር ተሰማ ተካ፣ደ/ር ገብሬ ይንቲሶ

Our Location

  • Sub Administration:
  • Address: Hawassa City
  • Phone:
  • Website: