"ቱሪዝም ለሁለንተናዊ እድገት!" በሚል መሪ ቃል የቱሪዝም ቀን እየተከበረ ነው!!

በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ42ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ ጊዜ የሚከበረው የቱሪዝም ቀን በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሐዋሳ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።

የኢፌዴሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው፣ የኢፌዴሪ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ ከፍተኛ የፌደራል የክልልና የከተማ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በፕሮግራሙ ተገኘተዋል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ ባስተላለፉት መልዕክት በዓሉ በሲዳማ ክልል መከበሩ ክልሉ ለቱሪዝም እና ኢንቨስትመንት ምቹ መሆኑን ለማስተዋወቅ ያግዛል ያሉ ሲሆን ክልሉ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው ሊኖረው የሚገባውን አስተዋፅኦ ከፍ እንዲልና ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን ያደርጋል ብለዋል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር ሚንስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው ሀገራችን ኢትዮጵያ በምታደርገው የእድገት ጎዳና ለቱሪዝም ዘርፍ የሚኖረው ድርሻ የጎላ መሆኑን ገልጸው በዘንድሮ በሀገር ደረጃ ለ34ተኛ ጊዜ የሚከበረውን የቱሪዝም ቀን በሲዳማ ክልል እንዲከበር መወሰን የተቻለው በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ያለውን ባህልና መልካም እሴት ፣ መልካም የመሬት አቀማመጥ እንዲሁም መስህቦችን ለማስተዋወቅና ቱሪዝምን በመሳብ ነው ብለዋል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ የቱሪዝም አምባሣደር በመሆነ የተሽለሙ ሲሆን በተመሣሣይ መልኩ ዩኒቨርስቲዎች፣ ኮሌጆች፣ አስጎብኚ ድርጅቶች፣ ሆቴሎች እና ለግልለሰቦች የኢትዮጵያን ቱሪዝም እንዲስትሪ በማስተዋወቅ ተፅዕኖ በመፍጠራቸው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስተር እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

በመጨረሻም "ቱሪዝም ለሁለንተናዊ እድገት" በሚል የእለቱን ፕሮግራም በማስመልከት በሲዳማ ክልል ገጽታ የሚያሣይ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቧል።

ሐ/ከ/አሐ/ከ/አ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ

መስከረም 14/2013 ዓ.ም

ሐዋሳ

Share this Post