"የከተማችን ውበት ግብር ከፋዮቻችን ናቸው" በሚል መሪ ቃል የገቢ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ነው የንቅናቄ መድረኩ የተካሄደው።

በንቅናቄ መድረኩ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማ ም/ከንቲባና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ሚልክያስ በትሬ ከተማዋን ይበልጥ ተመራጭና ተወዳዳሪ ከተማ ለማድረግ ግብር ከፋዮች ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ እንደመሆኑ የመድረኩ አስፈላጊነትን ያጎላዋል ብለዋል።

የሐዋሳን ከተማ ልማትና ዕድገት ይበልጥ ለማፋጠን በከተማው የገቢ አሰባሰብና አስተዳደር ሥራዎች ላይ በሚስተዋሉ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሀሳቦች ላይ መምከሩ አስፈላጊ እንደሆነ የገለፁት ደግሞ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምሩ ተፈሪ ናቸው።

እንደ ኃላፊው ገለፃ ከግብር ከፋዮች የሚነሱ ሀሳቦች እንደ ግብዓት በመውሰድ እና መፍትሄ በመስጠት በቅንጅት መሥራት ለተሻለ ውጤታማነት ተኪ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አስምረዋል።

በምክክር መድረኩ ላለፋት አምስት አመታት የግብር አሰባሰብ የሚገጽ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን የመድረኩ ተሣታፊዎች በበኩላቸው መንግስት ህገ-ወጥ የጎዳና ንግድን በመከላከል ህጋዊ ሆነው መስራት እንዲችሉ ማድረግ እንዳለበት ገልጸዋል።

ግብር ከፋይ ነጋዴዎችን በአግባቡ እንዲከፍሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በየጊዜው መስጠት እንዳለበትም ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል።

በመጨረሻም በአንዳንድ ግብር ከፋዮች ዘንድ የሚስተዋለውን ለሸጡት ዕቃና ለሰጡት አገልግሎት ደረሰኝ ያለመስጠት ችግር በማስወገድ ለበጀት ዓመቱ የታቀደን ብር 2.6 ቢልዮን ዕቅድ ስኬታማነት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ የመድረኩ ተሳታፊዎች ቃል በመግባት መድረኩ ተጠናቅቋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ጥቅምት 3/2014 ዓ.ም

ሐዋሳ

Share this Post