ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚደረገውን ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የታቦር ክ/ከተማ የሴቶች አደረጃጀት አስታወቀ።

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የታቦር ክ/ከተማ አስተዳደር የሴቶች መደራጃ እድር እና የልማት ቡድን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አድርገዋል።

የሐዋሣ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች መምሪያ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ በአሁኑ ወቅት እንደሀገር የገጠመንን ችግር ለመወጣት እናቶች በገንዘብም በጉልበትም በመደገፍ ለሠራዊቱ አንድነታቸውን እየገለጽ እንደሚገኙ ተናግረዋ።

ወ/ሮ አይናለም ወ/ሰንበት የታቦር ክ/ከተማ ሴቶች ሊግ ኃላፊ በክ/ከተማ ከዚህ በፊት በገንዘብ እና በአይነት የተለያዩ ድጋፎች ማደረጉን ገልጸው በዛሬው እለትም በሶ 17 ኩምታል እንዲሁም የተለያዩ አልባሳትና የፍጆታ እቃዎች ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።

ተሣታፊዎች እናቶች በበኩላቸው ከምናደርገው የገንዘብም ሆነ የአይነት ድጋፍ በተጨማሪ በቦታው ድረስ በመሄድ በመዝመት ሀገራችንን እንጠብቃለን በማለት አንድነታቸውን ገልጸዋል።

የሐ//አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ህዳር 14/2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post