ለአርቲስት አዱኛ ዱሞ የክብር ዶክተሬት ተሰጠ!!

በዛሬው ዕለት ከ6800 በላይ ምሩቃንን ያስመረቀው የሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በሲዳማ ህዝብ የትግል ታሪክ በአርቱ ዘርፍ ትልቅ አስተዋፅኦ ሲያበረክት ለቆየው አርቲስት አዱኛ ዱሞ የክብር ዶክተሬት አበርክቷል።

አርቲስት አዱኛ ዱሞ ልብ ውስጥ በሚቀርና ወዝወዝ በሚያደርጉ ዜማ እና ግጥሞቹ የህዝቡን ማህበራዊ ሁኔታና አኗኗር በማዜምና ለህዝቡ ነፃንነት ሲታገል የኖረ ብርቅዬ የሲዳማ ልጅ ሲሆን ለሲዳሙ አፎ ዘፈን ፈር ቀዳጅና ለወጣት አርቲስቶች ምሳሌ ነው።

የክብር ዶክተር አርቲስት አዱኛ ዱሞ በሲዳምኛ ቋንቋ(ሲዳሙ አፎ) የሚያቀነቅነው ስለወጣበት ህዝብ ማንነት ብቻ ሳይሆን ስለሀገሩ ሰላምና አንድነት በተለያዩ ሀገራዊና ሌሎች ቋንቋዎች በተለያዩ ወቅቶች ስለሚፈጠሩ ህዝባዊ አጀንዳዎች ቀደም ብሎ መልዕክት የማስተላለፍ አቅም ያላቸውን አስተማሪ ሰራዎቹን ለአድናቂዎቹ አድርሷል።

አንጋፋውና የሲዳማ ፈርጥ ተወዳጁ አርቲስት ለሀገር በተለያየ መልኩ ባበረከተው ጉልህ አስተዋፅኦ በዛሬው ዕለት የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ተወያይቶ ባፀደቁት መሠረት የክብር ዶክተሬት ተበርክቶለታል።

ለክቡር ዶክተር አርቲስት አዱኛ ዱሞ፣ ለወዳጅ ዘመድ እና አድናቂዎች እንዲሁም ለመላው የሲዳማ ህዝብ የእንኳን ደስ አለን!!

የሐ/ከ/አስ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ

መስከረም 8/01/2014 ዓ.ም

ሐዋሳ

Share this Post