02
Dec
2021
በግንባር ተገኝተው በአንደኛው የጦር ግንባር የመጨረሻ ዕቅድ ላይ የመከሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአጠረ ጊዜና በአነስተኛ መሥዋዕትነት የኢትዮጵያ ድል የሚረጋገጥበትን መመሪያ ሰጥተዋል።
ሠራዊቱ በከፍተኛ ሞራል ላይ እንደሚገኝና ጠላትም እየተሸነፈ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጡ ሲሆን ÷ በተደናበረ ዕቅድ የገባው ጠላት ተደናብሮ መውጣት እንደማይችል ተናግረዋል።
ለአሸባሪው ዓላማ የተሰለፉ ሁሉ እጃቸውን በመስጠት ራሳቸውን እንዲያተርፉ፣ የትግራይ ወላጆችም ልጆቻችን የት ደረሱ ብለው እንዲጠይቁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።
‘’የኢትዮጵያ ፍላጎት ሰላምና ልማት ነው። ወደዚህ ጦርነት የገባነው ተገድደን ነው። ማሸነፋችን ግን አይቀሬ ነው’’ ሲሉ የኢትዮጵያን ድል አድራጊነት ገልጠዋል።
የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ህዳር 21/2014 ዓ/ም
ሐዋሳ
ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ