ለጋራ ሀገራዊ ጉዳይ በጋራ መቆም እንደሚያስፈልግ የሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ትሴ ተናገሩ።

በሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ የ2014 ዓ/ም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ለ16ኛ ጊዜ ሲከበር የጸረሙስና ቀንም ተከብሯል።

የክ/ከተማው ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ይህ በዓል ህብረብሄራዊነትን በማጠናከር በወንድማማችነት እሴት ለጋራ ሀገራዊ ጉዳይ በጋራ መቆምን የሚያጎለብት ነው ብለዋል።

አቶ ብርሃኑ አክለውም ከተማችን የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ መሆኗን ገልጸው ይህ ደግሞ የቆምንለትን አንድ ዓላማ ማሳካት የሚያስችልና ጎን ለግን በተሰማራንበት የስራ መስክ ልማትን ለማፋጠን የሚያግዝ ነውም ብለዋል።

ሀገርን የሚጎዳና ልማትን የሚያቀጭጭ ሙስናንም እያስተማርንና እያወገዝን መቀነስ እንደሚገባ የተናገሩት አቶ ብርሃኑ አሁን በሀገራችን ላለው ክስተት ኢትዮጵያዊያን ከየአቅጣጫው እያደረጉት ያለው ምላሽና ድጋፍ ለሀገር ጉዳይ በጋራ መቆምን አመላካች ነውና ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም የብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት ተከብሮ መኖር በሀገር ልማት ላይም አሻራቸውን ለማሳረፍ የሚያስችል ነው ብለዋል።

አካባቢያችንን በንቃት በመጠበቅ ጭምር ለሀገራችን ነጻነት በጋራ እንቆማለንም ብለዋል ተሳታፊዎቹ።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ህዳር 21 2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post