ራህማ መስጊድ

በሐዋሳ ከተማ በተለምዶ አረብ ሰፈር ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የራህማ መስጊድ በከተማው የመጀመሪያ የእስልምና ሃይማኖት ተቋም ሲሆን የተመሠረተውም በ1953 ዓ.ም ነው፡፡

በወቅቱ ከዲላ ከተማ የመጡ አረብ ሙስሊሞች በአካባቢው ሰፍረው በመኖራቸው ምክንያት ነው የአካባቢው መጠሪያ “አረብ ሠፈር” የተባለው፡፡

እነዚህ ሠፋሪዎች በመስጊድ ምስረታ ወቅት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳበረከቱ ይነገራል፡፡ ለመስጊድ ግንባታ የሚሆነውን ቦታ አስፈቅደው የተረከቡት ሀጂ ሙስሊማኖ የተባሉ ግለሰብ ሲሆኑ ሀጂ ዓሊ ዘለቀ የተባሉ ግለሰብ ደግሞ በግንባታው ወቅት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳበረከቱም ነው የሚነገረው፡፡

አነስተኛ የነበረው የመስጊድ ህንጻ በአዲስ መልክ የተገነባው በ1967 ዓ.ም ሲሆን እስከአሁን ድረስም አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ነው፡፡

የራህማ መስጊድ በማህበራዊ ዘርፍ የጎላ ድርሻ እያበረከተ ስለመሆኑ በተቋሙ አማካይነት የተመሠረተው ኑር የትምህርት ማዕከል ተጠቃሽ ነው፡፡

የሐ/ከ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ነሐሴ 15/2013

ሐዋሳ

ምንጭ፡- የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ባ/ቱ/ስ/መምሪያ

Share this Post