07
Dec
2021
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ለተቋሙ ሰራተኞች በካይዘን ፍልስፍናና በBSC ዕቅድ ዝግጅት ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥቷል።
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ሀላፊ አቶ ገዛኸኝ ወ/ሰንበት በእጃችን ያሉ ውጤቶችን ከጣልነው ግብ አንጻር ውጤታማ ለማድረግ ስልጠናው አጋዥ ነው ብለዋል።
በካይዘን ፍልስፍና ተግባራትን እያከናወንን እንገኛለን ያሉት አቶ ገዛኸኝ ያሉብንን ጉድለቶች አርመን ስኬታማነታችንን ለመጨመር መድረኩ እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ሰራተኛው በእቅድ ዝግጅት ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ይዞ እንዲተገብር ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንም ነው አቶ ገዛኘኝ ያከሉት።
የተቋሙ የልማት እቅድ ቡድን መሪ አቶ ዘነበ ቱማቶ እና ሌሎች ባለሙያዎች ስልጠናው የነበረብንን ጉድለት የሚምላና ለምንሰራው ስራ ውጤታማነት ወሳኝ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ባለሙያዎቹ አክለውም በየጊዜው በቂ ግንዛቤ እንድናገኝ መደረጉ ባገኘነው እውቀት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችል ነው ብለዋል።
የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ህዳር 28/2014 ዓ/ም
ሐዋሳ