በሐዋሳ ሚሊኒየም አደባባይ የ2014 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የምግብ ማጋራት ኘሮግራም ተካሄደ!!

በበጎ ተግባር በተሰማራው ቢኒያም አለማየሁ(ልጅ ቢኒያም) አማካኝነት ከ1000 በላይ የሆኑ የጎዳና ልጆችና ለችግር የተጋለጡ ወገኖች ሲሆኑ በምገባ ኘሮግራሙ ላይ የተሳተፉት በቀጣይም በራሱ ተነሳሽነት ማዕድ የማጋራትና የስራ ዕድል የመፍጠር እቅድ እንዳለውም ተገልጿል። የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ካሱ አሩሳ ይህ በጎ ተግባር በተለይም በለውጡ መንግስት ትኩረት የተሰጠው ተግባር ሆኖ እየተሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን እነዚህን ወገኖች መንከባከብና በሀገር ልማት ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ ደግሞ ከሁሉም የሚጠበቅ ተግባር ነው ብለዋል አቶ ካሱ ። የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ አቶ ደግፌ ዳንኤል ይህ ጉዳይ ለመንግስት ብቻ የሚተው አለመሆኑን ገልጸው እያንዳንዱ ሰው አቅም በፈቀደ መጠን ወገኑን ለማገዝ ቢነሳ ችግሮችን ማቃለል ይቻላል ብለዋል። የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ፍሬሕይወት ወ/ጻዲቅ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ የጎዳና ወጣቶችን ወደስራ ለማሰማራት ከሚያደርገው ጥረት ጎን ለጎን በበጎ ተግባር ላይ የሚሰማሩ ግለሰቦችም ድርሻቸው የላቀ በመሆኑ ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል። የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ መስከረም 6/2014 ዓ/ም ሐዋሳ

Share this Post