በሐዋሳ አተማ አስተዳደር በሐይቅ ዳር ክ/ከተማ 16ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ተከበረ።

"ወንድማማችነት ለህብረብሄራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል ነው በዓሉ የተከበረው።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ አረጋ ባርሳ መድረኩን በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት ሀገራችን በአጣብቂኝ ውስጥ ባለችበትና የሀገሪቱ ቁንጮ መሪ ሀገርን ከመበታተን ለማዳን በጦር ግንባር መሆናቸው የዘንድሮውን በዓል ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

አቶ አረጋ አክለውም ህገ መንግስቱ ብሄር ብሄረሰቦች ሁሉም እኩል መሆናቸውን ቢያረጋግጥም የጋራ ታሪክና እሴት ያላትን ኢትዮጵያ በአካባቢ ድንበር በማበጀትና በመከፋፈል ጁንታው ለረጅም ጊዜ ሲያታልል የቆየበት መሆኑን አንስተዋል።

የውስጥና የውጭ ሀይሎች እየሰነዘሩ ያለው ጥቃት ኢትዮጸጵያን ለማፍረስ ነው ያሉት አቶ አረጋ በወንድማማችነት መንፈስ የጋራ እሴቶችን ገንብተን የተደቀነብንን አደጋ መቋቋም ስለምንችል ከየትኛውም ጊዜ በላይ የተጠናከረ አንድነት ሊኖረን ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ ስለኢትዮጵያዊነት፣ ወንድማማችነት እና መሪ ቃሉ ላይ ያተኮረ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን በቀረበ ጥያቄና ሀሳብ ውይይት ተደርጎበታል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በአገር ሉዓላዊነት የማይደራደሩ መሆኑን ሲገልጹ መንግስት ለሚያቀርበው የትኛውም ምላሽ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ህዳር 22/2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post