በታቦር ተራራ እና በሐዋሳ ሀይቅ ዳርቻ ዙሪያ በ2014 ዓ/ም ለማስጀመር በታቀደ ኘሮጀክት ጥናት ዙሪያ የተደረገውን ውይይት የመሩት የክልሉ ፕሬዚደንት አቶ ደስታ ሌዳሞ ናቸው።
ይህ የ7.25 km ኘሮጀክት በስድስት ደረጃ ተከፋፍሎ በተለዩ ቦታዎች የሚተገበር ሲሆን 1.6 ቢሊየን በላይ የሚፈጅ መሆኑም ተገልጿል።
የኘሮጀክቱ ስራ በአረንጓዴ ልማት ያሸበረቁና ልዩ ልዩ ዘመናዊ የመዝናኛ ቦታዎች የተካተቱበት ሲሆንበታቦር ተራራ እና በሐዋሳ ሀይቅ ዙሪያ የሚተገበረው ይህ ልዩ ኘሮጀክት ለከተማዋ ተጨማሪ ዕድገት ነው ተብሏል።
ይህ ኘሮጀክት የከተማዋን አረንጓዴ ውበት፣ እድገት፣የቱሪስት ፍሰት ከፍ ከማድረጉ በተጨማሪ ገቢን ከማሳደግና የከተማዋን ተመራጭነት ከማጉላት አንጻር እንደ ሀገርም የጎላ ሚና ያለው ነው ያሉት የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ናቸው።
ኘሮጀክቱ የህዝብ ነው፣ ከተባበርንም ማሳካት እንችላለን ያሉ ሲሆን ከከተማዋ ህዝብ፣ ከባለሀብቶች፣ ከምሁራን፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሁሉ ውይይት የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።
ስለ ኘሮጀክቱ ገለጻ ከቀረበ በኃላ ክቡር ፕሬዚደንቱን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በሰጡት አስተያየት ይህ ኘሮጀክት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሚፈጸም በመሆኑ የተነሱ ተጨማሪ ሀሳቦችም የዲዛይኑ አካል ሆነው በተሻለ ፍጥነትና ጥራት መከናወን አለበት ብለዋል።
በውይይት መድረኩ የተሳተፉ አመራሮች ኘሮጀክቱን አስመልክቶ በቀረበው ገለፃ እጅግ መደሰታቸውን ገልፀውይህ ኘሮጀክት ለከተማው የሚኖረው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጠቀሜታ የጎላ በመሆኑ ለኘሮጀክቱ መሳካት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁነታቸውን ገልፀዋል።
የሐ/ከ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ነሀሴ 8/ 2013 ዓ/ም
ሐዋሳ