በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር በምስራቅ ክፍለ ከተማ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

በክፍለ ከተማው የውቅሮ ቀበሌ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚውል የምግብ ድጋፍ ነው ያደረጉት።

የሐዋሣ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት ወ/ሰንበት ህብረተሰቡ ለሀገር መከላከያ በገንዘብም በጉልበትም የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የክ/ከተማው ሴቶች ሊግ ኃላፊ ወ/ሮ ዝናሽ አሰፋ በውቁሮ ቀበሌ የሚገኙ እናቶች ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ 6 ኩንታል በሶ፣ 1 ኩንታል ዳቦ ቆሎ በማዘጋጀት ከዚህም በተጨማሪ አልባሳት እንዲሁም የፍጆታ እቃዎችን ድጋፍ እንደተደረገ ተናግረዋል።

በድጋፉ የተሳተፉ እናቶች በበኩላቸው ከምናደርገው የገንዘብም ሆነ የአይነት ድጋፍ በተጨማሪ በቦታው ድረስ በመሄድ በመዝመት የበኩላችንን እንወጣለን በማለት ተናግረዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ህዳር 14/2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post