02
Aug
2021
የሀይማኖት አባቶች፣ምእምናን፣ ወጣቶችና የታቦር ክ/ከተማ አመራሮች በችግኝ ተከላው ተሳትፈዋል።
የታቦር ቃለ ህይወት ቤ/ክ የሽማግሌዎች ሰብሳቢ አት እስራኤል ባፌ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመረ አረንጓዴ አሻራ ተግባር በቤተክርሲቲያኗ ለ2ኛ ጊዜ መፈጸሙን ተናግረው ይህም ምድርን መንከባከብና ማሳመር ለሰው ልጆች የተሰጠ አደራ ነው ብለዋል።
የታቦር ክ/ከተማ ቃለህይወት ቤ/ክ ፓስተር አበራ ሰጦሬ ምድርን የማልማት ሀሳቡ መጽሀፍ ቅዱሣዊ መሆኑን ገልጸው መትከል ብቻም ሳይሆን ተንከባክበን የለማች ምድርን ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይገባል ብለዋል።
በሐዋሳ ከተማ የታቦር ክ/ከተማ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ፍቅሬ በበኩላቸው የሀይማኖት ተቋማት ለመንግስት ጥሪ አፋጣኝ መላሽ እየሰጡ መሆኑን ገልጸው ከዚህ በተጨማሪ በመንግስት ያልተሸፈኑ የልማት ስራዎችን በመሸፈን የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ ይገኛሉ ብለዋል።
አቶ ታደሰ አክለውም እንደ ክ/ከተማ የተጀመረው የችግኝ ተከላ ስራ በሌሎችም የሀይማኖት ተቋማት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋለ።