በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የቱላ ክ/ከተማ ከተማ እናቶች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የደረቅ ምግብ ድጋፍ አደረጉ።

የሐዋሳ ከተማ ብልጽግና ጽ/ቤት ሴቶች ሊግ ወ/ሮ ጸሐይ ከንባታ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ብለው የሚያናፍሱት ግለሰቦች ከአልባልታ ወሬ እንዲቆጠቡ አሳስበው አንድነታችን ተጠናክሮ ወደ ብልጽግና ከፍታ እንወጣለን ሲሉም ተናግረዋል።

የሐዋሣ ከተማ አስተዳደር የቱላ ክ/ከተማ ሴቶች ሊግ ወ/ሮ ሰብለ ሜጋ በበኩላቸው የክ/ከተማው እናቶች እቤት ለቤት በመዘዋወር ድጋፍ በመጠየቅ አስባስበው 5 ኩንታል ከግማሽ የበሶ እህል አልባሳት እንዲሁም የፍጆታ እቃዎችን ድጋፍ እንዳደረጉ ገልጸዋል።

በዝግጅቱ ወቅት ያገኘናቸው እናቶች አሁን ከምናደርገው ድጋፍ በተጨማሪ አስፈላጊ ሲሆን ወደ ግንባር ድረስ ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ህዳር 14/2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post