በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የታቦር እና የሀይቅ ዳር ክ/ከተማ በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረጉ!!

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የታቦር ክ/ከተማ የዱሜ ቀበሌ አቦ የሴቶች መጀረጃ እድር እና በሀይቅ ዳር ክ/ከተማ የሁለቱም ቀበሌ የሴት አደረጃጀቶች በጁንታው ህወሓት ዕኩይ ተግባር ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ የአማራ እና የአፋር ክልል ነዋሪዎች በዛሬው እለት የሰበሰቡትን ድጋፍ ለክ/ከተማው ገቢ አድርገዋል።

በሁለቱም ክፍለ ከተሞች ያሉ የሴት አደረጃጀቶች እና የመረዳጃ እድሮች ካደረጉት ድጋፍ መሀከል በገንዘብ ሲተመን የታቦር ክ/ከተማ ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር የሚያወጣ የተለያዩ አልባሳት ፣ የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ፣ የጤፍ፣ የበቆሎ ዱቄት፣መኮሮኒ፣ፖስታ፣ እሩዝ እንዲሁም ሳሙና በእድሩ ተወካይ አማካኝነት ለወ/ሮ ጸሐይ ከንባታ የሐዋሳ ከተማ ሴቶች ሊግ ኃላፊ ያስረከቡ ሲሆን የሀይቅ ዳር ክፍለ ከተማ 500 ሺህ ብር በሚገመት ወጪ ነው ድጋፉን ያደረጉት።

በክ/ከተማው የሚገኙ የእድር ማህበራት፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ ወጣቶች፣ በቀበሌው ስር ያሉ የልማት ቡድኖችና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችን በማስተባበር ድጋፍ እንደተደረገ የገለፁት ወ/ሮ ተዋበች ተሻለ የታቦር ክ/ከተማ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጽ/ቤት ኃላፊ ናቸው።

የክ/ከተማው የሴቶች አጀረጃጀት ለሁለተኛ ዙር ድጋፍ ማድረጉን ገልጸው። ሌሎችም ድጋፍ በማድረግ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበው ለተደረገው ልገሳ በክ/ከተማው ስም አመስግነዋል።

ድጋፉን ያበረከቱት የሴት ተወካዮች ይህን ድጋፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዳሰባሰቡ ገልጸው። የተደረገው እርዳታ በቂ ባይሆንም አንድነታችንን ለመግለጽ ይረዳናል ብለዋል።

ሐ/ከ/አሐ/ከ/አ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ

መስከረም 13/2014 ዓ.ም

ሐዋሳ

Share this Post