በሐዋሳ ከተማ የሚገኘውን የናም ኮምፖስት ፕሮጀክቶች አስመልክቶ ከአምስት ከተሞች የተውጣጡ አካላት የልምድ ልውውጥ አደረጉ

በኢፌዲሪ ስራና ከተማ ልማት ሚንስትር የከተሞች ተጽእኖ መቋቋመያ ቢሮ ኃላፊና የናማ ኮምፖስት ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት ዳሪክተር ወ/ሪት ትእግስት በከተሞች በከፍተኛ ደረጃ የሚታየውን የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ችግርን ለመፍታት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በዚህ ረገድ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ከተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅትና ግሎባል ኢንቫይሮመንታል ፋሲሊቲ ጋር በመተባበር ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በተመረጡ ስድስት የኢትዮጵያ ከተሞች የናማ ኮምፖስት ፕሮጀክትን ተግባራዊ እያደረገ እደሚገኝም ነው ዳይሬክተሯ የተናገሩት፡፡

በዚህም እንደ ሀገር ፕሮጄክቱ ተግባራዊ ከተደረገባቸው ከተሞች ውስጥ በሐዋሳ ከተማ ያለው አፈፃፀም አበረታች እንደሆነም ተናግረዋል።

ይህ በሐዋሳ ከተማ ያለውን አበረታች ተግባር በሌሎች ከተሞችም ለማስፋት ይቻል ዘንድ የልምድ ልውውጥ መደረጉን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት መምሪያ ም/ኃላፊ አቶ ታሪኩ ታመነ በከተሞች የሚታየውን የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ችግሮችን ለመፍታት አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ተግባሩ በዋናነትም ከተማዋን ለነዋሪዎቻቸው ውብ ፅዱና ምቹ ማድረግ ስለመሆኑ የተናገሩት ሀላፊው በዚህም በከተማ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ በመታገዝ ከዳር ለማድረስ ጥረት እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል።

በዚህ ረገድ እንደ ሐዋሳ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት በተለይም ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ መከናወናቸው ስራውን ዘላቂ እንዲሆን እንዳስቻለውም ነው አቶ ታሪኩ የገለፁት።

በልምድ ልውውጡ የተሳተፉ የአዳማ፣ ድሬዳዋ፣ ባህር ዳርና ቢሾፍቱ ከተሞች ስለመሆናቸውም ከዳይሬክተሯ ገለፃ መረዳት ተችሏል።

በዚህ በከተሞች የልምድ ልውውጥ ላይ የሐዋሳ ከተማ የናማ ኮምፖስት ፕሮጄክት አስተባባሪ አቶ ኡርጌ አለሙ አጠቃላይ በከተማዋ እየተተገበረ ያለውን የፕሮጄክቱን አፈፃፀም አስመልክቶ ሪፖርት አቅርበዋል።

የፕሮጄክቱን አፈፃፀምም አስመልክቶ ከቀረበው ሪፖርት መነሻ በተጨባጭ ያለውን ሂደት አስመልክቶ የየከተሞቹ ተወካዮች በከተማዋ በመዘዋወር ተመልክተዋል።

በልምድ ልውውጡ ተሳታፊ የሆኑ የየከተሞቹ ባለሙያዎች በበኩላቸው እንደ ሐዋሣ ከተማ በኮምፖስት ናም ፕሮጄክት መሰረት የተከናወኑ ተግባራት በከተማቸው ተሞክሮውን በመውሰድ ለማስፋት የተለየ አጋጣሚ እንደፈጠረላቸውም ተናግረዋል።

በከተማዋ የናማ ኮምፖስት ፕሮጀክትን ተግባራዊ በማድረግ በተለይም አረንጓዴ ልማትን ስራዎችን በምን አግባብ ተግባራዊ እንደተደረገ የተመለከቱት ስራን ጨምሮ በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ረገድ ያለው የተቀናጀ ጥረት ውጤታማ እንዳደረገም መመልከታቸውን ተናግረዋል።

የሐ/ከ/አስየመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ታህሳስ 4/2014 ዓ.ም

ሐዋሳ

Share this Post