ውቧ፣ ጽዱና ማራኪዋ ከተማ ሐዋሳ በሀገራችን በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ ከተሞች መካከል ቀዳሚውን ተርታ ይዛለች፡፡
የነዋሪውን ተሳትፎ ባማከለ መልኩ በተሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች የውስጥና የውጭ ባለሀብቶችን በመሳብ የምትታወቅ፣ለመኖሪያ ምቹ፣ የኢንቨስትመንት ማዕከልና የቱሪዝም መዳረሻ ከተማም መሆን ችላለች ሐዋሳ፡፡
በከተማዋና አካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ ለበርካታ አመታት የዳበረ አብሮነት፣ መከባበር፣ አንድነና ሰላሟ ለሌሎች የሀገራችን ከተሞች እንደ መልካም ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድ ነው።
በዚህም የቤተሰባዊነት አቀባበል በፍቅር ከተማነት የምትታወቅ ስመ ጥር ከተማ እንድትሆንም አስችሏታል፡፡
የግል ኢንቨስትመንትን መሳብ ትኩረት ያደረገው ከተማ አስተዳደሩና የለውጡ አመራር ደረጃውን የጠበቀ መሰረተ ልማት ማስፋፋትና የፋይናንስ አቅርቦት ማነቆን ከመፍታት ረገድ ምቹ ሁኔታ መኖሩን ይገልጻል።
በአካባቢው ለፕሮጀክት ግንባታ በቂ ጥሬ ዕቃ መኖር፣ ከተማዋ ከአ/አበባ በቅርብ ርቀት መገኘት፣ በቂ የሰው ሀይል፣ ሰፊ የገበያ አድማስ መኖርና ሌሎችም ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ እድል የሚፈጥር ነው።
አርሶ አደሩ የሚያቀርበው የግብርና ምርት፣ የታቦር ኢኮ ቱሪዝምና የሐይቅ ዳርቻ ልማትም ሌላኛው ማሳያ ነው።
የኢንቨስትንመንት መሬት ዝግጁነት ከቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ጋር የዘርፉን ስኬቶች ምቹ ያደርጉታል፡፡
የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ ሐዋሳ ጨርቃጨርቅ፣ በቅድመ ትግበራ ሂደት ላይ የሚገኘው አማ ቢዝነስ ግሩፕ፣ አየር ማረፍያ፣ ከሞጆ ሐዋሳ ፈጣን መንገድኔ ሌሎችም ለአብነት የሚጠቀሱ ምቹ ሁኔታዎችና መልካም ዕድሎች አመላካች ናቸው፡፡
አስተዳደሩ ለግሉ ኢንቨስትመንት መስፋፋትና ለድህነት ቅነሳ አጋዥ ለሆኑና አሻራ ላሳረፉ ነባር ባለሀብቶች እንቁዎች ብቻም ሳይሆኑ አምባሳደሮች በማለት አክብሮቱን ይገልጻል፡፡
የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት አማራጮች ከሆኑት አምራች ዘርፍ፣ ሪል ስቴት፣ በሆቴልና በሎጅ፤ በከተማ ግብርና፣ በአገልግሎት ዘርፍ… ወዘተ በመሰማራት ኢንቨስት እንዲያደርጉና ከልማቱም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከተማ አስተዳደሩ አክብሮታዊ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ይምጡ ሐዋሳ ላይ ኢንቨስት በማድረግ የበለጠ ይበልጽጉ!
ለሀገራችን ብልጽግናም ወሳኝ መሰረት ይጣሉ!
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ጽ/ቤት!
የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
መስከረም 4/2013 ዓ/ም
ሐዋሳ