መድረጉ ለሁለት ቀናት የሚቆይ መሆኑም ታውቋል።
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረ/ኘሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ከተከበሩ ም/ቤት አባላት በ2013 ዓ/ም እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና በ2014 ዓ/ም ጠቋሚ እቅድ የቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየት በቀጣይ ለምንሰራው ስራ እንደ ግብዓት የሚያገለግል ነው ብለዋል።
ረ/ኘሮፌሰር ፀጋዬ እንደ ችግር ከተነሱ መካከል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት በከተማዋ ህግ የማስከበርና ህገወጥ ንግዶችን በመከላከል ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በሐገራችን ላይ ያንጃበበውን ችግር ኢትዮጵያዊያን በጋራ ሆነን የምንመክተው ሲሆን እንደከተማችን ተጨባጭም በየሰፈሩ ያሉ የአሸባሪውን አጀንዳ የሚያስፈጽሙ አካላትን በንቃት መጠበቅ ያስፈልጋል ነው ያሉት ከንቲባው።
የሐዋሳ ከተማ ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ደምሴ ዳንጊሶ በበኩላቸው በ2013 ዓ/ም በከተማዋ የተከናወኑ ተግባራት የሚገመገምበት መድረክ መሆኑን ገልጸው በዚህም ጠንካራ ጎኖችን እያስቀጠልን ክፍተቶችን የምናርበት ነው ብለዋል።
የተከበሩ የም/ቤት አባላት የም/ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ክትትልና ድጋፍ፣ ተጀምረው የቆዩ ኘሮጀክቶች መጠናቀቅ፣ ከፍተኛ ገንዘብ የወጣበት የዉሃ ኘሮጀክት አገልግሎት መስጠት እና የበርካታ መንገዶች መሰራት በጥንካሬ የሚገለጽ መሆኑን ተናግረዋል።
የተከበሩ የም/ቤት አባላት አክለውም ያልተደፈኑ የውሃ መውረጃ ቦዬች፣ ህገወጥ ግንባታ፣ የአገልግሎት አሳጣጥ ችግር መኖር እና ለረጅም ጊዜ ታጥረው ያልለሙ ቦታዎችን እንደ ጉድለት አንስተዋል።
የሐ/ከ/አሰ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ነሐሴ 15/2013
ሐዋሳ