ሐዋሳ ከተማ የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ "ፊቼ ጫምባላላን"ጨምሮ በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችና ባህላዊ እንዲሁም ሐይማኖታዊ በዓላትን የምታስተናግድ ውብ ከተማ ነች።
እነዚህን በርካታ ቅርሶቻችንን የምናስቃኝበት መርሀ-ግብር ያዘጋጀን በመሆኑ ለዛሬ የከተማችን አንዱ መስህብ የሆነውን "የሐዋሳ ደብረ- ምህረት ቅዱስ ገብርኤል (ገዳም) ቤተክርስቲያን" በጨረፍታ እናስተዋውቅዎ!!
በማራኪ ኪነ -ሕንጻው የሚታወቀው የሐዋሳ ደብረ- ምህረት ቅዱስ ገብርኤል (ገዳም) ቤተክርስቲያን
የመጀመሪያው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በሐዋሳ ከተማ በ1995 ዓ/ም ተቋቋመ፡፡ በ1976 ዓ.ም በአቡነ ተክለ ሀይማኖት ፖትሪያርክነት ዘመን በሐዋሳ ከተማ እንብርት /ፒያሳ/ ላይ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡
ለበርካታ አመታት አገልግሎት ሲሰጥ ከቆየ በኃላም በ1995 ዓ/ም በአዲስ መልክ ተገነባ፡፡ የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በአመት ሁለት ጊዜ በታህሳስ 19 እና ሐምሌ 19 በድምቀት ይከበራል፡፡
የከተማዋ ሰላምና የአየር ፀባይ ምቹነት ተደማምረው በብዛት ወደ ከተማው የሚተመው ምእምናን በአሉን በተሻለ እንዲከበርና ለቱሪስት ፍሰትና ለኢንዱስትሪው ዘርፍ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት መስፋፋት የራሱን አስተዋጽዕኦ እያደረገ ይገኛል፡፡
በተዋበ የህንጻ ዲዛይንና ጥበብ ዳግም የተሠራው ይህ ማራኪ ቤተክርስቲያን ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትም አጎናፅፏታል፡፡
የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከታህሳስ 19 እና ሐምሌ 19 ከንግስ መንፈሳዊ አገልግሎት በተጨማሪ የሐዋሳ ቤተ-ክህነት ትምህርት ቤት በቤተክርስቲያኒቱ መመስረት ለከተማው ህብረተሰብ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ህንፃዎችንም በመገንባትና በማከራየት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳው የጎላ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
የገብርኤል በዓል አከባበርና እሴትነቱ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳው ከከተማዋ ነዋሪና ለሃይማኖቱ ተከታይ ከሚኖረው ጠቀሜታ በዘለለ የውጭና የሀገር ውስጥ ታዳሚዎች የሚሳተፉበት በመሆኑ እንደ ሐዋሳ ከተማም ሆነ እንደ ሀገር ትልቅ ቦታ የሚሰጠውና በአግባቡ ሊጠበቅ የሚገባው ነው፡፡
የሐ/ከ/አስ/መን/ኮ/ጉ/መምሪያ
ነሀሴ7/2013ዓ.ም
ሐዋሳ
ምንጭ:-የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ባህል/ቱ/ስ/መምሪያ የቅርስ ጥ/ል/ የስራ ሂደት