በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሐዋሳ ከተማ የፖሊዮ ክትባት በይፋ ተጀመረ፡፡ :

በመርሀ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ጸጋዬ ቱኬ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ ለህፃናትና እናቶች ጤና ተኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።

በሚቀጥሉት አራት ቀናትም እንደ ሀገር ለሚሰጠው የፖሊዮ ክትባት ዘመቻም መላው የከተማዋ ነዋሪ ህፃናትን እንዲያስከትቡ ከንቲባው ተናግረዋል።

የጤና ሚኒስትር ዴኢታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ መርሀ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት ለህፃናት የጤና ሁኔታ መረጋገጥ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።

እንደ አህጉር በተለይም ህጻናትን የሚያጠቃው የፖሊዮ በሽታ አጎራባች ሀገራት በመከሰቱ ምክንያት የከፋ ጉዳት በሀገራችን ሳያስከትል መከላከል ተገቢ በመሆኑ ክትባቱ በይፋ ተጀምሯል ብለዋል።

በዚህም አሉ ሚንስትር ዲኢታው ዛሬ በሐዋሳ በይፋ የተጀመረው የፖሊዮ ክትባት ከጥቅምት 12-15 ቀን 2014 ዓ/ም በመላው ሀገራችን በተጠናከረ መልኩ የሚሰጥ ይሆናል።

በእነዚህ ቀናት በማሰጠው ክትባት ወላጆች ከአምስት አመት በታች ልጆቻቸውን ማስከተብ እንደሚገባቸውም ነው ሚንስትሩ የተናገሩተት።

በእነዚህ ቀናትም ወላጆች እራሳቸውን ከኮኖና ቫይረስ በመከላከል ተግባራዊ እንዲያደርጉም ነው ሚንስትሩ የተናገሩት።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሠላማዊት መንገሻ የክትባት ዘመቻው ቤት ለቤት በጤና ባለሙያዎች እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

እድሜአቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ከዚህ በፊት የፖሊዮ ክትባት ቢከተቡም ባይከተቡም ይህንን ክትባት መከተብ እንደሚገባቸውም ነው የቢሮ ሀላፊዋ የገለፁት፡፡

በክልሉ ስምንት መቶ ሺህ በላይ ህጻናት ክትባቱን እንደሚሰጥ የተናገሩት ዶ/ር ሰላማዊት ከፖሊዮ ዘመቻው ጎን ለጎን የኩፍኝና የሌሎች በሽታዎች ቅኝት እንደሚደረግም ጠቁመዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ጥቅምት 12/2014 ዓ.ም

ሐዋሳ

Share this Post