በሐዋሳ ከተማ ለሚሠሩ መሠረተ ልማቶች እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ከይዞታቸው ለተፈናቀሉ የማህበረሰብ ክፍሎች በኢኮኖሚ ለማቋቋም የሙያና ኢንተርፕረነርሽፕ ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የገጠር ሥራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ የገጠር ዘርፍ ም/ኃላፊና የገጠር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሐደራ ሐርቃ ገልጸውልናል።
በቱላ ክ/ከተማ የሚገኙ አራት(4) የገጠር ቀበሌያት ማለትም ቱሎ፣አላሙራ፣ጫፌ ኮቴጃዌሳ እንዲሁም ዳቶ ቀበሌያት ላይ ልየታ በማድረግ በግብርና በንግድ ዘርፍ በማህበር በማደረጃት በመረጡት ፓኬጅ መሠረትት በፕሮጀክቱ የተመቻቸላቸውን ገንዘብ ወስጀው ወደ ሥራ እንደሚገቡና የማምረቻ እና የመሸጫ ቦታ በመንግስት በኩል ድጋፍና ክትትል እንሚደረግላቸው ኃላፊው ተናግረዋል።
የሴቶች ማረፊያ ልማት /AWSAD/ እና የጥላ ፕሮጀክት አስተባባሪ ወ/ሮ ራሔል መስፍን በበኩላቸው ይህ ፕሮጀክት በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እንደሚሰራ ገልጸው።
በቱላ ክ/ከተማ ከላይ በተጠቀሱ አራት ቀበሌያት 1,350 ሰዎች ስልጠና ወስደው ወደሥራ እንድገቡ እና የራሳቸውን ገቢ እንዲያገኙ ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል።
የስልጠና ተሣታፊዎቹ በበኩላቸው ይህን እድል በማግኘታቸው ደስተኛ እንደሆኑ የገለጽ ሲሆን ከስልጠናው በኋላ በሚሠማሩበት የሥራ መስክ ውጤታማ በመሆን ሌሎችም የሥራ እድል እንደሚፈጥሩ ተናግረዋል።
በዚህ ፕሮጀክት 75% ሴቶች እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን ስልጠናው ለስድስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይም ታውቋል ።
ሐ/ከ/አሐ/ከ/አ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ነሐሴ 18/2013 ዓ.ም
ሐዋሳ