በዛሬው እለት በአራት ክ/ከተሞች ታቦር፣ ሐዌላ ቱላ፣ ምስራቅና መሐል የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ እንደሆና በቀጣይ ቀናትም የቀሩ ክ/ከተሞች እንደሚቀጥል የገለጹት አቶ ደስታ ዳንኤል የትምህርት መምሪያ ኃላፊ ናቸው።
የትምህርት ጥራት ላይ ያለውን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ አመራሩ፣ የሕብረተሰብ፣ ተሳትፎ እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ በየደረጃው ያለው የዘርፍ አመራር፣ ሕዝቡ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች በማሣተፍ እቅዱን በሚገባ ማሳካት እንደሚቻል አቶ ደስታ ተናግረዋል።
በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን 64 ሺህ በላይ ተቀብሎ ለማስተማር በእቅድ እንደተያዘ ገልጸው።
ወላጆች እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆችን ወደ ት/ቤት መላክ እንዳለባቸው የታቦር ክ/ከተማ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ፍቅሬ ገልጸዋል።
የመማር ማስተማሩ ምቹ እንዲሆን ባለድርሻ አካላት ከመንግስት ጋር በመቀናጀት መስራት እንደሚገባ አቶ ብርሐኑ ትሴ የሐዌላ ቱላ ክ/ከተማ አስተዳዳሪ ገልጸው ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠትም ክትትልና ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
በመድረኩ የትምህርት አመራርና ባለድርሻ አካላት ተሣትፈዋል።
ተሣታፊዎች በበኩላቸው የታቀደውምን እቅድ ለማሳካት እንደሚሠሩና በመማር ማስተማሩም ተግባር ላይ ከመንግስት ጎን በመሆን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተከናወኑ ተግባራቶችንና ያጋጠሙ ችግሮችን እንዲሁም የ2014 ዓ.ም የንቅናቄ ሰነድና እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከነሐሴ 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ መዝገባ እንደሚ ጀመር ተገልጿል።
ሐ/ከ/አሐ/ከ/አ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ነሐሴ 21/2013 ዓ.ም
ሐዋሳ