በስፖርት አጀረጃጀት፣ ገቢ አሰባሰብና አጠቃቀም ዙሪያ ውይይት ተደረገ!!

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አማካኝነት በስፖርት አጀረጃጀት፣ ገቢ አሰባሰብና አጠቃቀም ዙሪያ ከክ/ከተማ አመራሮችና ከባለድርሻ አካለት ጋር ግንዛቤ ሚያስጨብጥ ውይይት ተደረገ።

በአካልና በአዕምሮ የዳበረ ወጣት ከማፍራት ባለፈ ብቃት ያለው ስፖርተኛን በማብዛት ክፍለ ከተሞችን፣ከተማችንን ብሎም ሀገራችንን በዘርፉ ሊያስጠሩ የሚችሉ ስፖርተኞችን ለማፍራት መሠራት እንዳለበት አቶ ታሪኩ ሾኔ የሐዋሳ ከተማ ብልጽግና ፖርቲ አደረጃጀት ኃላፊ ገልፀዋል።

ኃላፊው አክለውም ስፖርት ዘርፉ ማህበራዊ መሰረቱን ህዝባዊ በማድረግ ከመንግስት የበጀት ድጎማ በተጨማሪ የራሱ የገቢ ምንጭ እንዲኖረው ክትትልና ድጋፍ እንደሚያስፈልገውም ተናግረዋል።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ደረጊቱ ጫሌ የስፖርት ዘርፉን ለማጠናከር ከተያዘው በጀት በተጨማሪ የገቢ ማሰባሰብ ስራውን እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በትኩረት መሰራት እንዳለበት ገልጸው። መምሪያውም ለዘርፉ ልዩ ተኩረት በመስጠት እየሠራ ነው ብለዋል።

አቶ ጥላሁን ሃሚሶ የባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ም/ኃላፊና የስፖርት ዘርፊ ኃላፊ በበኩላቸው ባለፈው አመት የተመዘገቡ ውጤቶች እንደተጠበቁ ሆኖ የማዘውተሪያ ስፍራዎችን በማዘመንና የተጀመሩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማስቀጠል መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በስፖርት አጀረጃጀት፣ ገቢ አሰባሰብና አጠቃቀም ዙሪያ በአቶ አቡሽ አለማየሁ ጹሑፋ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

መስከረም 5/2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post