በበዓለ ሲመቱ የተለያዩ የሀገር መሪዎች የተናገሩት መልዕክት፦

የኬኒያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ

"ኢትዮጵያ በአፍሪካ ብቸኛዋ በቅኝ ግዛት ያልተያዘች ሀገር ናት።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌት ሀገር ናት። ስለዚህ ኢትዮጵያ እናት ሀገራችን ናት። እናት ሀገር ጥሩ ሁኔታ ውስጥ ካልሆነች ሌሎች ሀገራትም ሰላም አይኖራቸውም"

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት

"ያለኢትዮጵያ ዛሬ ያለንበት መድረስ አይቻለንም ነበር።"

የጅቡቲው ፕሬዚደንት ኢስማኤል ኡመርጌሌህ

"ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህብረት መመስረት ፋና ወጊ ሀገር ናት

ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካን እንቅስቃሴ መስራችና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ናት። ኢትዮጵያ በታሪኳ ብዙ ችግሮች ቢያጋጥሟትም የሚገጥማትን ፈተና ሁሉ በራሷ መንገድ ትፈታቸዋለች፡፡ አሁንም ጠንካራ ሀገር ሆና ቀጥላለች ብለዋል።"

የዩጋንዳዉ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ

"ለአፍሪካዉያን ከጎሳ ፖለቲካ ይልቅ የአንድነትና የሃገራዊ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ እጅጉን አስፈላጊ ነው። ይህን ደግሞ ኢትዮጵያ አሁን እያሳየችን ነው ያለችው"

የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሀመዱ ቡሀሪ

"ሀገሪቱ በሰኔ ወር ያደረገችው ምርጫ ምን ያህል ዲሞክራሲያዊ ስለመሆኑ ይሄ አመላካች ነው። ሁሉም በሀገሪቱ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገረ ግንባታ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል።"

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

መስከረም 24/1/2014 ዓ.ም

ሐዋሳ

Share this Post