በከተማ ደረጃ የሚስተዋሉ የልማት የመልካም አስተዳደር እና የአካባቢ ጥበቃ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ዋጋ የሚከፍል አመራር መፍጠር ይጠይቃል ሲሉ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ገለፁ።

እንደ ከተማ የሚስተዋሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በተለይም ከከተማ ፅዳትና ውበት፣ እንዲሁም ከአረንጓዴ ልማት ስራዎች ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮችን ለቅሞ ለመፍታት ያለመ የውይይት መድረክ በየደረጃው የሚገኙ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር አመራር አካላት በተገኙበት በዛሬው እለት ተካሂዷል።

የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ፣ አቶ ካሱ አሩሳ የሐዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊን ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተደሩ የየደረጃው አመራር አካላት በተገኙበት በተካሄደው በዚሁ መድረክ በሰባት ክፍለ ከተሞች ከ20 በላይ በሚሆኑ ቀበሌያት የልማትና የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የፅዳትና ውበት እና አረንጓዴ ልማት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ተካሂዷል።

በመድረኩ በሰባት ክፍለ ከተሞች ከ20 በላይ በሚሆኑ ቀበሌያት የሚስተዋሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለቅሞ በወፍ በረር የሚያሳይ የተደራጀ መረጃ የቀረበ ሲሆን በየደረጃው የሚገኙና ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ችግሮቹን ለመፍታት የሚያስችል ሰፊ ውይይትም ተካሂዶበታል።

መድረኩን የመሩት ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በከተማ ደረጃ የሚስተዋሉና መሻገር ያልቻሉ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ለቅሞ ለመፍታትና ሙሉ በሙሉ ለመሻገር ዋጋ ከፍሎ የሚሰራ አመራር መፍጠር ላይ በልዩ ትኩረት ይሰራልም ብለዋል::

በተጨማሪም የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ለቅሞ ለመፍታት ህጋዊ አሰራርን መከተል፣ አደረጃጀቶችን ማጠናከርና፣ ማንቀሳቀስ እንዲሁም አስፈላጊውን ግብዓት በማሟላት የአጭርና የረዥም ጊዜ እቅድ አውጥቶ ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ እየሰጡ መሄድ እንደምገባ ተገልጿል።

ከነዋሪው ህብረተሰብ ጋር በቅንጅት ከሰራን እንደ ከተማ የሚስተዋል የትኛውም ችግር ከኛ የመፍታት አቅም በታች ነው ያሉት የመድረኩ ተሳታፊ አመራር አካላት በተነሳሽነት፣ በቅንጅትና በቁርጠኝነት በመስራት የነዋሪውን ጥያቄ ለመመለስ የሚጠበቅብንን ኃላፊነት እንወጣለንም ብለዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ጥቅምት9/2014 ዓ.ም

ሐዋሳ

Share this Post