በዓሉን ስናከብር የዘማች ቤተሰቦችን እያሰብን ሊሆን እንደሚገባ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰር ጸጋዬ ቱኬ ተናገሩ

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የመሐል ክ/ከተማ ማህራዊ ዘርፍ የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ለዘማች ቤተሰቦች ድጋፍ አድርጓል።

በዚህ በክፍለ ከተማው በተዘጋጀው የገና በዓልን የተመለከተ ድጋፍ 100 ለሚሆኑ ለዘማች ቤተሰቦች፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ለአረጋውያን የበግ፣ ዘይትና ዱቄት ተበርክቶላቸዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰር ጸጋዬ ቱኬ፣ አቶ ካሱ አሩሳ፣ አቶ ዘማች እርጥቤ፣ የማች ቤተሰቦች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኘተዋል።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰር ጸጋዬ ቱኬ ሁሉም ህብረተሰብ ለሀገር ህልውና ዘብ ለቆሙት የዘማች ቤተሰቦች የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ በማድረግ አሌኝታነቱን ማሣየት አለበት ብለዋል፡፡

እንደ ከንቲባው ገለፃ መረዳዳትና መደጋገፍ የህብረተሰቡ የቆየ ዕሴት በመሆኑ ይህ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የመሐል ክ/ከተማ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ትንሳኤ መሣይ በበኩላቸው የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ለራሳቸው ህይወት ሳይሳሱና ከቤተሰባቸው ተለይተው በህልዉና ዘመቻው ላይ ለተሳተፉ ቤተሰቦች ክ/ከተማው ድጋፍ እንዳደረገ ገልጸዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም የመከላከያ ሠራዊቱን ቤተሰብና አረጋዊያንን መጠየቅና መንከባከብ አገራዊ ፋይዳዉ የላቀ እንደሆነ ገልጸው የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ በዚህ ዘርፍ የተሳተፉትን ሁሉ ከልብ አመስግነዋል፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው የዘማች ቤተሰቦች ክ/ከተማው ባሳየው አጋርነት ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ታህሳስ 27/2014 ዓ.ም

ሐዋሳ

Share this Post