25
Oct
2021
ከንቲባው ከከተማው አመራር አካላት ጋር በመሆን የግሉን ዘርፍ የት/ት ተቋማት እና በኢንቨስትመንት የተሰማሩ የግል ድርጅቶችን ጎብኝተዋል።
በኢንፎኒክ ኮሌጅ ተገኝተው የጎበኙት ከንቲባው ኮሌጁ ከግቢ ውበት፣ ጽዳት፣ ምቹ የመማሪያ ክፍሎች እና በቴክኖሎጂ የታወቀ መሆኑ ለትምህርት ጥራት የሰጠውን ትኩረት ማሳያ ነው ብለዋል።
በኮሌጁ የታየው መልካም ልምድ ለሌሎችም ተቋማት የሚጠቅም መሆኑን የተናገሩት ከንቲባው የከተማዋን አገልግሎት አሰጣጥም በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ ከኮሌጁ ጋር ተቀራርበን የምንሰራ ይሆናል ብለዋል።
ከግል ኢንቨስትመንት ዘርፍ የጉብኝቱ አካል የሆነው ግ.ሪን ማርክ ሄርቢስ በአረንጓዴ ቅጠል ምርቶች ላይ የሚሰራ ሲሆን ይህንንም ከሀገር ውጪ በመላክ በኢኮኖሚው ዘርፍ የበኩሉን ሚና እየተወጣ ያለ መሆኑ ተገልጿል።
ጉብኝት የተደረገባቸው የግሉ ዘርፍ ሀላፊዎች በበኩላቸው የተሻለ ምርታማ ለመሆን ተግዳሮት ናቸው ያሏቸውን ጥያቄዎች ለክቡር ከንቲባው አቅርበዋል።
የተከበሩ ከንቲባም ከተቋማቱ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት አስተዳደሩ ያለውን ፍላጎት ገልጸው አቅም በፈቀደ መጠን የቀረቡ ጥያቄዎች የሚፈቱ መሆኑን ተናግረዋል።
የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ጥቅምት 12/2014 ዓ/ም
ሐዋሳ