በ2013 በጀት ዓመት በክፍለ ከተማ ደረጃ ለ5300 ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የታቦር ክፍለ ከተማ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ፍቅሬ ገለፁ።

በ2013 በጀት ዓመት በክፍለ ከተማ ደረጃ ለ5300 ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የታቦር ክፍለ ከተማ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ፍቅሬ ገለፁ።

በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የታቦር ክፍለ ከተማ የስራ እድል ፈጠራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት እንዲሁም የክፍለከተማው የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ባንክ የ2013 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2014 በጀት ዓመት እቅድ የባለድርሻ አካላት የንቅናቄ መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

በመድረኩ በክፍለ ከተማው ስራ ዕድል ፈጠራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት አማካኝነት በ2013 በጀት ዓመት ከ5300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ የገለፁት አቶ ታደሰ ህብረተሰቡን፣ በየደረጃው ያሉ አመራር አካላትን እና ባለሙያውን በማስተባበር በ2014 በጀት ዓመት ከዚህ የላቀ ቁጥር ያላቸውን ነዋሪዎች የስራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በቁርጠኝነት ይሰራልም ብለዋል።

የክፍለከተማው ስራ ዕድል ፈጠራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን ደሳለኝ በበኩላቸው እንደ ክፍለ ከተማ ልለዩኒቨርስቲ ምሩቃን፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለስደት ተመላሾችና ለአጠቃላይ ስራ ፈላጊ ዜጎች ትኩረት በመስጠት መሰራቱን ገልፀው በበጀት ዓመቱ ከተያዘው ዕቅድ አኳያ 75% ማሳካት መቻሉንም ጠቁመዋል።

በበጀት ዓመቱ በቀበሌ ደረጃ የስራ ፈላጊ ልየታ ስራ በመስራት በኮንስትራክሽን፣ በኢንዱስትሪ፣ በከተማ ግብርና፣ በአገልግሎት ዘርፍ በመንግስትና በግል ተቋማት ቅጥር እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች በቋሚነት የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መስፍን ጠቁመዋል።

በዛሬው መድረክ የክፍለከተማው ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ባንክ 2013 በጀት ዓመት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን አቶ ጥላሁን በጢሶ የክፍለከተማው ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ በሁሉም የብድር አይነቶች 22ሚሊየን ብር በብድር በማሰራጨት ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።

የቁጠባ ስራዎችን በተመለከተ የውስጥ አቅምን በማጠናከር በተሰራ ስራ የተሻለ አፈፃፀም አስመዝግበናል ያሉት አቶ ጥላሁን ከብድር አመላለስ አንፃር አሁንም ሰፊ ክፍተት መኖሩን ነው የጠቆሙት።

ከ2009 ዓም ጀምሮ በወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ 137 ማህበራት 22ሚሊየን ብር በብድር መሰራጨቱን አቶ ጥላሁን ጠቁመው ከዚህም ውስጥ 1.2ሚሊየን ብር ብቻ ተመላሽ መሆኑን እና የተቀረው ገንዘብ ከ1 እስከ 3 ወር ውዝፍ ውስጥ የገባ መሆኑንም አመላክተዋል።

ከክፍለከተማው ስፋት እና ካለው ምቹ ሁኔታ አንፃር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ረገድ ያልተጠቀምንባቸው ብዙ ዕድሎች አሉ ያሉት አቶ ታደሰ ፍቅሬ በዛሬው ዕለት ባደረግነው ግምገማ ከስራ ዕድል ፈጠራ አንፃር እንዲሁም ከቁጠባ፣ ብድር ስርጭትና፣ አመላለስ አኳያ ጠንካራ አፈፃፀሞችን ለማስቀጠል እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችን ለይተን በያዝነው በጀት ዓመት ለተሻለ አፈፃፀም በሙሉ አቅማችን ለመንቀሳቀስ ባለድርሻ አካላት መግባባት ላይ ደርሰናልም ብለዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ጥቅምት/6/2014 ዓ.ም

ሐዋሳ

Share this Post