በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስራች ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አድርጎ መረጠ

አቶ ታገሰ ጫፎ ላለፉት ሶስት አመታት የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ በመሆንም ያገለገሉ ናቸው።

በተመሳሳይም ምክር ቤቱ ወይዘሮ ሎሚ በድኦን ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ መርጧል።

ወ/ሮ ሎሚ በድኦ ቀደም ሲል የጨፌ ኦሮሚያ ዋና አፈ ጉባኤ ሆነው ያገለገሉ ናቸው።

የተመረጡት ሁለቱም የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤዎች በጉባኤው ፊት ቀርበው ቃለ መሀላም ፈፅመዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

መስከረም 24/1/2014 ዓ.ም

ሐዋሳ

Share this Post