ትልቁ ዋርካ ወደቀ

ከምንም ተነስተው አንቱ የተባሉ ባለሀብት ነበሩ፤ አቶ በሹ ቱሉ።

እኚህ በግጭት ወቅት አስታራቂ፣ በሰላም ወቅት የልማት አርበኛ የሆኑትን አባት ህልፈተ ሞት መስማት እጅግ ያማል።

ለሐዋሳችንም ድምቀት የነበሩ ጋሽ በሹ ባለሀብት ብቻም አልነበሩም ከወጣት ጋር ልብን የሚያሸፍት ተስፋን በማቀበል፣ ከእኩዮቻቸው ጋር ለሀገር መፍትሄ አፈላላጊ፣ ከመንግስት ጋር የልማት አርበኛ በመሆን ነበር ኖረው ያለፉት።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደርም በእኚህ ሁለገብ አባት ህልፈተ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለመላው ቤተሰባቸውና ዘመድ አዝማዳቸው መፅናናትን ይመኛል።

የሐ/ከ/አስ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ነሔሴ 15/2013 ዓ.ም

ሐዋሳ

Share this Post