አመታዊው የኢትዮጵያ የሐዋሪያት ቤተክርስቲያን ኮንፍረንስ በደማቅ ሁኔታ በሐዋሳ እየተከበረ ይገኛል!!!

የሐዋሳ ከተማ ከምታስተናግዳቸው ሀይማኖታዊ ክብረበዓላት አንዱ ነው የሐዋሪያት ቤተክርስቲያን አመታዊ ክብረ በዓል።

በዚህ ግዙፍ በዓል ላይ በመገኘትም ነው የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ለምዕመኑ እና ለሀይማኖት አባቶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልካም ምኞታቸውን አቅርበዋል።

በበዓሉ ለመታደም ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የሀይማኖቱ ተከታዮችን ቆይታቸው ያማረ እና መንፈሳዊ በረከትን የሚቀበሉበት እንዲሆንም ጭምር ነው ከንቲባው በመልዕክታቸው የገለፁት።

የሐዋሳ ከተማ መሰል ግዙፍ ሀይማኖታዊ በዓላትን በተለያዩ ጊዜያት ስለማክበሯም ያስታወሱት ከንቲባው ይህም የከተማዋን ለዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች ተመራጭ የሚያደርጋት እንደሚሆን ተናግረዋል።

Share this Post